ኢየሱሴ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ (Eyesusie Ende Ante Yale) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yoseph Bekele)

Lyrics.jpg


(2)

ማህተሜን ፡ የፈታህ
(Mahetemien Yefetah)

ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yoseph Bekele)

 
መከራ ፡ ሲበዛ ፡ ቀንም ፡ ሲጨላልም
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የምትሆን ፡ ወንድም ፡ አዎ
የተዘጋውን ፡ በር ፡ ደርሰህ ፡ ትከፍታለህ
ከድሃው ፡ ጐን ፡ ኢየሱስ ፡ ትቆምለታለህ ፡ አዎ

የምስኪኖች ፡ ወዳጅ ፡ ኢየሱስ ፡ የተጣለን ፡ ምታነሳ
ቸር ፡ አምላክ??? ፡ በክብር ፡ ምታኖር ፡ አበሳውን ፡ ምታስረሳ
አቤት ፡ አቤት ፡ ጌታዬ ፡ እንደአንተ ፡ ያለ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ማንም ፡ የለም (አቤት ፡ አቤት)
አቤት ፡ አቤት ፡ አባባ ፡ እንደአንተ ፡ ያለ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ አዎ

አንተው ፡ ብቻ ፡ አባቴ ፡ ነህ ፡ አንተው ፡ ብቻ ፡ ጌታ
አንተው ፡ ብቻ ፡ ወዳጄ ፡ ነህ ፡ አንተው ፡ ብቻ ፡ ጌታ
አንተው ፡ ብቻ ፡ አሃሃ ፡ አንተው ፡ ብቻ ፡ አዎ
አንተው ፡ ብቻ ፡ እውነተኛ ፡ አንተው ፡ ብቻ ፡ ኢየሱስ

ዘመን ፡ ቢከፋም ፡ እኔስ ፡ አምንሃለሁ
አንተ ፡ እኮ ፡ ከያዝከኝ ፡ እንዳልወድቅ ፡ አውቃለሁ ፡ አዎ
የማምለጫ ፡ አለት ፡ መሸሻ ፡ አምባዬ
የክፉ ፡ ቀን ፡ ወዳጅ ፡ ለእኔስ ፡ መጠጊያዬ ፡ አዎ

ዝርግፍ ፡ ጌጤ ፡ ምኮራብህ ፡ አለኝ ፡ ብዬ ፡ ምመካብህ
አንተው ፡ ብቻ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ በራሴ ፡ ላይ ፡ ዛሬም ፡ ሾምኩህ
አቤት ፡ አቤት ፡ ኢየሱሴ ፡ እንደአንተ ፡ ያለ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ማንም ፡ የለም (አቤት ፡ አቤት)
አቤት ፡ አቤት ፡ አባቴ ፡ እንደአንተ ፡ ያለ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ አዎ

አንተው ፡ ብቻ ፡ መኩራዬ ፡ ነህ ፡ አንተው ፡ ብቻ ፡ ጌታ
አንተው ፡ ብቻ ፡ ዝርግፍ ፡ ጌጤ ፡ አንተው ፡ ብቻ ፡ ጌታ
አንተው ፡ ብቻ ፡ አሃሃ ፡ አንተው ፡ ብቻ ፡ ኢየሱስ
አንተው ፡ ብቻ ፡ እውነተኛ ፡ አንተው ፡ ብቻ ፡ ኢየሱስ

ሰባራውን ፡ ልቤን ፡ አንተው ፡ ጠገንክልኝ
ሸክሜን ፡ ከላይ ፡ አንከባለልክልኝ ፡ አዎ
ዛሬ ፡ ይኸው ፡ ቀና ፡ አልኩኝ ፡ በአንተ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አርነት ፡ ወጣሁኝ ፡ መቆዘኔ ፡ አበቃ ፡ አዎ

የልቤ ፡ ወዳጅ ፡ ሚስጥረኛ ፡ የጓዳዬን ፡ ምታውቅልኝ
አቤት ፡ በአንተ ፡ ስንቱን ፡ አለፍኩ ፡ ኢየሱሴ ፡ ክበርልኝ
አቤት ፡ አቤት ፡ ጌታዬ ፡ እንደአንተ ፡ ያለ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ማንም ፡ የለም (አቤት ፡ አቤት)
አቤት ፡ አቤት ፡ አባባ ፡ እንደአንተ ፡ ያለ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ አዎ

በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ለቅሶዬን ፡ ሰምተሃል
እምባዬን ፡ አብሰህ ፡ ሳቅ ፡ አርገህልኛል
አስጨናቂዎቼ ፡ ዛሬ ፡ ይኸው ፡ አፈሩ
አንተ ፡ የሰራኸውን ፡ ማዳንህን ፡ አዩ ፡ አዎ

ማን ፡ እንደአንተ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ እስራትን ፡ የሚፈታ
ቀንበር ፡ ሰብሮ ፡ የሚያሳርፍ ፡ ለቅሶውን ፡ ደግሞ ፡ በደስታ
አቤት ፡ አቤት ፡ ኢየሱሴ ፡ እንደአንተ ፡ ያለ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ማንም ፡ የለም (አቤት ፡ አቤት)
አቤት ፡ አቤት ፡ አባባ ፡ እንደአንተ ፡ ያለ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ አዎ

ቸርነትህን ፡ ምህረትህን ፡ በሕይወቴ ፡ አይቻለሁ
ራራህልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ያለፈውን ፡ ረስቻለሁ
ስብራቴን ፡ ጠግነኸው ፡ ቀና ፡ አድርገህ ፡ አራመድከኝ
ቁሻሻዬን ፡ አስወግደህ ፡ ንጹህ ፡ ልቤስን ፡ አለበስከኝ

አንተው ፡ ብቻ ፡ ግነህልኝ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ግነህልኝ
ዛሬም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ መኩራዬ ፡ የዘለዓለም ፡ ማረፊያዬ
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ እንደገና
ለጌታ ፡ ለአምላኬ ፡ ይገባዋልና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ እንደገና
ለጌታ ፡ ለአባቴ ፡ ይገባዋልና

ኢየሱሴ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ጉልበቴ ፡ ነህ ፡ እወድሃለሁ
አንተ ፡ አለቴ ፡ መድሃኒቴ ፡ አምባዬ ፡ ነህ ፡ አመልክሃለሁ
ስትረዳኝ ፡ ስታግዘኝ ፡ ስታጽናናኝ ፡ አየሁ ፡ በዐይኔ
ምን ፡ እላለሁ ፡ ማዳንህን ፡ አወራለሁ ፡ በዘመኔ

አንተው ፡ ብቻ ፡ ግነህልኝ??? ፡ የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ግነህልኝ
ዛሬም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ መኩራዬ ፡ የዘለዓለም ፡ ማረፊያዬ
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ እንደገና
ለጌታ ፡ ለአምላኬ ፡ ይገባዋልና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ እንደገና
ለጌታ ፡ ለአባቴ ፡ ይገባዋልና

ብርና ፡ ወርቅ ፡ አልማዝ ፡ ዕንቁ ፡ ቀይም ፡ ዘምቤል ፡ አያክል
ለእኔ ፡ እኮ ፡ አንተ ፡ ከዚም ፡ በላይ
ታበራለህ ፡ ውብ ፡ እኮ ፡ ነህ
ደም ፡ ግባቴ ፡ ዛሬም ፡ ጥርሴ
ሞገሴ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ላመስግንህ ፡ በዝማሬ ፡ በሆታና ፡ በዕልልታ

አንተው ፡ ብቻ ፡ ግነህልኝ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ግነህልኝ
ዛሬም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ መኩራዬ ፡ የዘለዓለም ፡ ማረፊያዬ ፡ ሃሌሉያ
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ እንደገና
ለጌታ ፡ ለአምላኬ ፡ ይገባዋልና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ እንደገና
ለጌታ ፡ ለአባቴ ፡ ይገባዋልና


Navigation menu