ቸርነትህን ፡ አዜማለሁ (Cherenetehen Aziemalehu) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yoseph Bekele)

Lyrics.jpg

(2)

ማህተሜን ፡ የፈታህ
(Mahetemien Yefetah)

ቁጥር (Track):

(5)

ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yoseph Bekele)

አዝ፦ አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፤ ቃላቶች ፡ ያጥሩኛል ፡ የምልህ
ምሥጋናን ፡ ሁልጊዜ ፡ አበዛለሁ ፤ ቸርነትህን ፡ አዜማለሁ
አምላኬ ፡ አንተን ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፤ እገዛልሃለሁ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
አባቴ ፡ አንተን ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፤ እኔ ፡ አመልክሃለሁ ፡ በደስታ

ተስፋ ፡ ያደረኩት ፡ ያመንኩት ፡ ሲከዳኝ
አስፈሪው ፡ ጨለማም ፡ ዙሪያዬን ፡ ሲከበኝ
ነፍሴ ፡ ስትጨነቅ ፡ ደረስህ ፡ ወዳጄ
ጨለማዬም ፡ በራ ፡ ተዋበልኝ ፡ ደጄ
ላንግስህ ፡ ሰግቼ ፡ ኢየሱስ ፡ ላንግስህ ፡ ሰግቼ

አዝ፦ አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፤ ቃላቶች ፡ ያጥሩኛል ፡ የምልህ
ምሥጋናን ፡ ሁልጊዜ ፡ አበዛለሁ ፤ ቸርነትህን ፡ አዜማለሁ
አምላኬ ፡ አንተን ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፤ እገዛልሃለሁ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
አባቴ ፡ አንተን ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፤ እኔ ፡ አመልክሃለሁ ፡ በደስታ

የተሰበረውን ፡ ስብራቱን ፡ ጠጋኝ
የታመመን ፡ ፈዋሽ ፡ ያዘነውን ፡ አጽናኝ
ከእናት ፡ ከአባት ፡ በላይ ፡ ደርሰህ ፡ ትረዳለህ
የምስኪኑ ፡ አባት ፡ መጠጊያው ፡ አንተ ፡ ነህ
ዛሬም ፡ ላሞጋግስህ ፡ ኢየሱስ ፡ ዛሬም ፡ ላሞጋግስህ

አዝ፦ አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፤ ቃላቶች ፡ ያጥሩኛል ፡ የምልህ
ምሥጋናን ፡ ሁልጊዜ ፡ አበዛለሁ ፤ ቸርነትህን ፡ አዜማለሁ
አምላኬ ፡ አንተን ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፤ እገዛልሃለሁ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
አባቴ ፡ አንተን ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፤ እኔ ፡ አመልክሃለሁ ፡ በደስታ

ወደላይ ፡ ብወጣም ፡ አንተ ፡ በዚያ ፡ አለህ
ወደታች ፡ ብወርድም ፡ በዚያም ፡ ትገኛለህ
በምድር ፡ ስፋት ፡ ሁሉ ፡ ያለውን ፡ የምታይ
እንደአንተ ፡ ማን ፡ አለ ፡ የሚኖር ፡ በሰማይ
አንተ ፡ ነህ ፡ የበላይ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የበላይ

አዝ፦ አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፤ ቃላቶች ፡ ያጥሩኛል ፡ የምልህ
ምሥጋናን ፡ ሁልጊዜ ፡ አበዛለሁ ፤ ቸርነትህን ፡ አዜማለሁ
አምላኬ ፡ አንተን ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፤ እገዛልሃለሁ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
አባቴ ፡ አንተን ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፤ እኔ ፡ አመልክሃለሁ ፡ በደስታ

Navigation menu