Yosef Bekele/Baleweletayie Gieta/Mesqeleh Ser

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

እናንተ ደካሞች ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋቹሃለሁ የማቴዎስ 11:28

ዘማሪ ዮሴፍ በቀለ ርዕስ መስቀልህ ስር አልበም ባለውለታዬ ጌታ

አዝ እስኪ መስቀልህ ስር ሸክሜን ልጣለው (፪x) ኦሆ ኦሆ ማረፊያዬ ኢየሱስ ሰላሜ በአንተ ነው እረፍቴ በአንተ ነው አዎ ሁሉ ያለቀበትን መስቀልክን እያየሁ (፪x) ኦሆ ኦሆ ያኔ መከራዬን ችግሬን እረሳለሁ ጭንቀቴን እረሳለሁ አዎ

ክላሲካል

በቀራኒዮ ላይ ስለእኔ ተሰቅለህ (፪x) ኦሆ ኦሆ አንተ በእኔ ፈንታ እርጉም ሰው ተብለህ (፪x) አዎ ተፈጸመ ብለህ ሁሉንም ጨረስከው (፪x) ኦሆ ለዘለዓለሙ መርገሜን ወሰድከው እዳዬን ከፈልከው አዎ

መራራውን ጽዋ ጠጣህ በእኔ ፈንታ የታሰርኩበትም ሰንሰለት ተፈታ መስቀልህ ስር አለሁ ጥያቄዬን ይዤ ከላዬ ውሰደው ኢየሱስ ወዳጄ

ክላሲካል

አዝ እስኪ መስቀልህ ስር ሸክሜን ልጣለው (፪x) አዎ ማረፊያዬ ኢየሱስ ሰላሜ በአንተ ነው እረፍቴ በአንተ ነው አዎ ሁሉ ያለቀበትን መስቀልክን እያየሁ (፪x) ኦሆ ኦሆ ያኔ መከራዬን ችግሬን እረሳለሁ ጭንቀቴን እረሳለሁ አዎ

ክላሲካል

ሸክም ሲያንገላታኝ ቀንበር ሲከብድብኝ (፪x) ኦሆ ኦሆ ጨለማው በርትቶ መሄጃው ሲጠፋኝ (፪x) አዎ ቀና ብዬ ሳይህ ስጠራህ ጌታዬ (፪x) ኦሆ ኦሆ ፈጥነህ ድረስና ስበርው ከላዬ ቀንበሩን ከላዬ አዎ

ከእናት ከአባት በላይ ቀርበህ ምትረዳኝ ሚስጢሬን ተካፋይ ማን እንደ አንተ ጌታ ገበናዬን ሸፋኝ ሚስጢረኛዬ ነህ ከማንም ከምንም ትበልጥብኛለህ ከታላቁ ስፍራ ከዛ የወረድከው ፍቅር ያስገደደህ ኦ ኢየሱስ ለእኔ ነው (፪X) ችግሬን ሚረዳኝ እንደ አንተ የለምና ሁሉን ነግርሃለሁ ፊትህ እደፋና።