Yosef Bekele/Baleweletayie Gieta/Abietu Endante Manew

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ዮሴፍ በቀለ ርዕስ አቤቱ እንዳንተ ማነው አልበም ባለውለታዬ ጌታ ዙሪያዬ ሲጨልምብኝ መሄጃው ግራ ሲገባኝ ዓይኖቼን ወዳንተ አቀናሁ ረዳቴን ፍጠንልኝ አልኩኝ አንተም አንጊዳጐድክና ጠላቴንም በተንክና ዳግም አጽንተህ አቆምከኝ ብርቱ ጦረኛም አረከኝ

አዝ በሃዘን ችግሬ ጊዜ አይዞህ ባይ ደራሽ አጋዤ ስጠራህ ጥነህ የምትደርስ ሳነባ እምባዬን ምታብስ አቤቱ እንዳንተ ማነው አባባ እንዳንተ ማነው አቤቱ እንዳንተ ማነው ኢየሱሴ እንዳንተ ማነው

ጠላቴ ፡ ወጥመድ ፡ ዘርግቶ ፡ በብርቱ ፡ ነፍሴን ፡ ፈልጐ ዙሪያዬን ፡ ሲዞር ፡ ሲያደባ ፡ ሲዶልት ፡ ከእጁ ፡ ሊያስገባ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጻድቅ ፡ ነህ ፡ በቅን ፡ የምትፈርድ ወጥመዱን ፡ ሰባበርክልኝ ፡ ከለላ ፡ እምባዬ ፡ ሆንክልኝ

አዝ በሃዘን ችግሬ ጊዜ አይዞህ ባይ ደራሽ አጋዤ ስጠራህ ፈጥነህ የምትደርስ ሳነባ እምባዬን ምታብስ አቤቱ እንዳንተ ማነው አባባ እንዳንተ ማነው አቤቱ እንዳንተ ማነው ኢየሱሴ እንዳንተ ማነው

በምክርህ አንተ ግሩም ነህ ሁሉን በፍቅር የያዝህ ምሬቴን ከእኔ አውጥተሃል በፍቅር ቃል አጽናንተኸኛል የሚጤስ ጧፌን ያበራህ ቅጥቅጥ ሸምበቆዬን ያጸናህ እንዳንተ ማን አለ ጌታ ምን ልክፈል ለአንተስ ውለታ

አዝ በሃዘን ችግሬ ጊዜ አይዞህ ባይ ደራሽ አጋዤ ስጠራህ ፈጥነህ የምትደርስ ሳነባ እምባዬን ምታብስ አቤቱ እንዳንተ ማነው አባባ እንዳንተ ማነው አቤቱ እንዳንተ ማነው ኢየሱሴ እንዳንተ ማነው

እንዳንተ ማነው ማን እንዳንተ ማነው አባባ ኢየሱስ እንዳንተ ማነው ማን እንዳንተ ማነው ለእኔ የደረሰው

አንተን ብዬ ስምህን ጠርቼ መቼ አፍሬ አውቃለሁ ጌታ አመልክሃለሁ ጧት ማታ

አመልክሃለሁ (፬x) አመልክሃለሁ (፬x)