Yohannes Girma/Amlakie Destayie/Amlakie Destayie

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ከቶውን ፡ በለስ ፡ ባያፈራ ወይንም ፡ ሀረግ ፡ ላይ ፡ ፍሬ ፡ ባይገኝ የወይራ ፡ ስራ ፡ ቢጐድል ፡ እርሾችም ፡ መብልን ፡ ባይሰጡ

እኔ ፡ ግን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ደስ ፡ ይለኛል በመድኃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ሀሴት ፡ አደርጋለሁ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ኃይሌ ፡ ነው እግሮቼን ፡ እንደ ፡ ዋላ ፡ እግሮች ፡ ያበረታል በከፍታዎች ፡ ላይ ፡ ያስኬደኛል ፡ (፪x)

አምላኬ ደስታዬ ደስታዬ ነህ ኢየሱሴ ሙላቴ እርካታዬ ነህ (፪x)

በቅተኸኛል ሌላም አልፈልግም ቀረ የምለው ነገርም የለኝም ታምኜብህ በሁሉ ነገሬ ይዤ መጣሁ የከንፈሬን ፍሬ (፪x)

ምን ይከብደው ብዬ ለየትኛው ልሥጋ ምን ያቅተውና ምኑን ብዬ ልፍራ (፪x)

ተራራ ላይ ማዳን የቻለው ሸለቆም ውስጥ ኃይል የእርሱ ነው ሁሉን ሚችል ሥሙም ኤልሻዳይ የእኔ አምላክ ያለ በሰማይ (፪x)

እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ከወዴት ፡ ይገኛል ለሕዝቡ ፡ መከታ ፡ ፅኑ ፡ ጋሻ ፡ ሆኖአል ፡ (፪x)

መመኪያ ፡ ነው ፡ ለትውልድ ፡ ትምህርት መጔደጃ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ኩራት የሚታመኑት ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይላሉ ለዘላለም ፡ ማዳኑን ፡ ያያሉ ፡ (፪x)