የአማርኛ ፡ ክርስትና ፡ ፊሞች (Christian Videos)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


Amharic Videos | Tigrinya Videos | Afaan Oromo Videos

የኢየሱስ ፡ ታሪክ (Jesus Film) (128 mins)

ይህ ፡ ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሕይወት ፡ የሚያስተምር ፡ "ኢየሱስ" ፡ የተባለ ፡ ፊልም ፡ ነው። እስከዛሬ ፡ ድረስ ፡ ይህ ፡ ፊልም ፡ ከተሰራበት ፡ ፲ ፺ ፻ ፹ ፮ ፡ አመተ ፡ ምህረት ፡ ጀምሮ ፡ ከ ፲ ፻ ፡ በላይ ፡ ወደሚሆኑ ፡ ቋንቋዎች ፡ ተተርግሟል። የእግዚአብሔር ፡ ወንጌል ፡ ለማድረስ ፡ በጣም ፡ ጠቃሚና ፡ አስፈላጊ ፡ የሆነ ፡ መሳሪያ ፡ ነው።

A docudrama on the life of Jesus Christ, the "JESUS" film has been translated into more than 1,100 languages since its 1979 release. It remains the most translated and viewed film in history. Pastor Rick Warren, author of "The Purpose Driven Life," says "The 'JESUS' film is the most effective evangelistic tool ever invented."


የኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ለህጻናት (Jesus Film For Children) (61 mins)

የኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ለህጻናት ፡ የእግዚአብሔር ፡ አብንና ፡ የኢየሱስን ፡ ወልድን ፡ እውነት ፡ ህጻናት ፡ እንዲረዱት ፡ ቀለል ፡ በላ ፡ መንገድ ፡ የተሰራ ፡ ፊልም ፡ ነው። ይህ ፡ ፊልም ፡ ፵ ፡ ደቂቃ ፡ የሚያህል ፡ ፊልም ፡ ከዋናው ፡ "ኢየሱስ" ፡ ከተባለው ፡ ፊልም ፡ ያካተተ ፡ ሲሆን ፡ በዚህም ፡ ወስት ፡ ወደ ፡ ፳፪ ፡ ደቂቃ ፡ ያህል ፡ አዳስ ፡ የ ፡ ስድስት ፡ ህጻናት ፡ ገለጻ ፡ ያካተተ ፡ ነው። ይህ ፡ ፊልም ፡ በህጻናት ፡ አመለካከት ፡ ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ሕይወትና ፡ ስራው ፡ የሚያስተምር ፡ ፊልም ፡ ነው።

"The Story of Jesus for Children" provides a solution to the challenge of teaching children the truth about God and His Son, Jesus. This film uses 40 minutes of the original "JESUS" film and integrates into the drama 22 minutes of new footage involving six children who might have lived during the time of Christ. Told from a child's point of view, this film provides an overview of Christ's life and ministry.


መቅደላዊት (Magdalena) (58 mins)

"መቅደላዊት" ፡ ለሴቶች ፡ የተሰራ ፡ ፊልም ፡ ሲሆን ፡ የእግዚአብሔርን ፡ ፍቅር ፡ እንዲሁም ፡ ወንጌል ፡ እያስተማረ ፡ የሴት ፡ እህቶችን ፡ ልብ ፡ እየነካ ፡ ሕይወትን ፡ ሊለውጥ ፡ የሚችል ፡ ፊልም ፡ ነው። የኢየሱስን ፡ ደግነት ፡ እንዲሁም ፡ ታሪካቂ ፡ ስራዎቹን ፡ በመቅደላዊት ፡ ማሪያም ፡ ዐይን ፡ እንደታዪ ፡ አርጐ ፡ ሚተርክ ፡ ፊልም ፡ ነው።

Magdalena, a film made especially for women, beautifully shares God's love and the gospel, engaging women at the heart level with the potential of changing their lives for eternity.

A story of tenderness, freedom and purpose, it portrays Jesus' compassion for women and historical accounts of His interactions with them, as seen through the eyes of Mary Magdalene.


የመጨረሻዬ ፡ ቀኔ (My Last Day) (9 mins)

ይህ ፡ የ፱ ፡ ደቂቃ ፡ ታሪክ ፡ ከኢየሱስ ፡ ከሚባለው ፡ ፊልም ፡ አንዳንድ ፡ ንግግሮችን ፡ እየተጠቀመ ፡ ልክ ፡ እንዴኢየሱስ ፡ ተሰቅሎ ፡ በምተ ፡ ወንጀለኛ ፡ ዐይን ፡ ለመመልከት ፡ የሚያስችለን ፡ ፊልም ፡ ነው። የወንጀለኛው ፡ ጸጸት ፡ የኢየሱስን ፡ ንጹህነትና ፡ ጥፋት ፡ የለሽነቱን ፡ እንዲረዳ ፡ ያደርገዋል። "የመጨረሻ ፡ ቀኔ" ፡ አጭር ፡ የጸጸት ፤ የንሰሃ እንዲሁም ፡ የመዳን ፡ ፊልም ፡ ሲሆን ፡ በጃፓናዊ ፡ በሆን ፡ የአሳሳል ፡ መንገድ ፡ የተሰራ ፡ ፊልም ፡ ነው።

This 9-minute story, which utilizes dialogue from the original "JESUS" film, unfolds through the eyes of a criminal who receives the same brutal crucifixion sentence as Christ. The criminal's own guilt causes him to realize Christ's innocence. "My Last Day" is a short film of regret, repentance and redemption that frames the story of salvation using Japanese-style animation to capture the attention of a new generation.


ፍለጋው (The Search) (7 mins)

ይህ ፡ አጭር ፡ ፊልም ፡ ስለ ፡ ወንጌል ፡ በቀጥታ ፡ ለማስተማር ፡ የተሰራ ፡ ሳይሆን፣ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ እንዴት ፡ ወንጌሉ ፡ በሕይወታችን ፡ እንደሚያስፈልገን ፡ ለመስተማር ፡ የተሰራ ፡ ነው። ይህን ፡ ከተመለከቱ ፡ በኋላ ፡ ስለ ፡ ራስዎ ፡ የሕይወት ፡ ታሪክና ፡ ስለ ፡ ተመለከቱት ፡ ሕይወት ፡ ከኢየሱስ ፡ ሕይወት ፡ ታሪክ ፡ ጋር ፡ ለማነጻጽር ፡ ይሞክሩ።

This short film is not intended to directly communicate the Gospel, but to facilitate a conversation that reveals our need for the gospel. After watching the film, look at the questions and talk about them. Think about how your own story and the stories of those you may be watching with connects with the story of the film and the story of Jesus.