Tesfaye Gabisso/Yenazretu Eyesus/Yenazretu Eyesus
ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ ርዕስ የናዝሬቱ ኢየሱስ አልበም የናዝሬቱ ኢየሱስ
ጊዜው ትዝ ይለናል የተጠራንበት ትዳሩን ሊያሸንፍ ሁሉም በያለበት ሲወጣና ሲወርድ አግኝተህ ስትጠራው አልማረክ ብሎ "እምቢ" ያለ ማነው
አዝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ከእኛ ጋራ ያለኸው የሚናወጠውን ወጀብ በሥልጣንህ ያዘዝከው ሥምህ አይጠገብ ደግመን ብንወድሰው
ደንቆሮዎች የነበርን መልካም ዜና ሰማን ከብርና ከወርቅ መብለጥህን ተረዳን ሙታን ስታስነሳ እውር ስታበራ ዓይናችን አይቶሃል ድንቅ ሥራ ስትሰራ
አዝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ከእኛ ጋራ ያለኸው የሚናወጠውን ወጀብ በሥልጣንህ ያዘዝከው ሥምህ አይጠገብ ደግመን ብንወድሰው
ከአንተ ጋር ስንጓዝ በዓለም ማዕበል ውስጥ ነፋሱን ገሰጽከው እኛ እንዳንሰምጥ ድምፅህ አይዘነጋም ያ የሚያጽናናው ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ለጠወለገ ሰው
አዝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ከእኛ ጋራ ያለኸው የሚናወጠውን ወጀብ በሥልጣንህ ያዘዝከው ሥምህ አይጠገብ ደግመን ብንወድሰው