Tesfaye Gabisso/Yenazretu Eyesus/Selewededkegn Wedehalew

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ለምን ወደድከኝ አልልህም በእርግጥ ወደኸኛል
የፍቅርህ መግለጫ ይሄ ነው ለእኔ ተወግተሃል
አንተ ለእኔ የሆንከውን ያህል እኔ ለአንተ አልሆንኩም
ምን ያህል እንደሆነ አላውቅም ለክቼ አላየሁም
ግን አንድ ነገር አውቃለሁ
ስለወደድከኝ ወድሃለሁ (፪x)

አዝ
ከእርግማን ስለ ዋጀኸኝ ሞተህ ሸክሜን ስለ ወሰድክ
በመንፈስ ቅዱስ ስለ ሞላኸኝ ነፍሴን ስለ ባረክ
ፀጋህን አብዝተህ ስለ ሰጠኸኝ ከቶም ስላልተውከኝ

ምን ያህል እንደሆነ አላውቅም ለክቼም አላየሁም
ግን አንድ ነገር አውቃለሁ
ስለወደድከኝ ወድሃለሁ (፪x)

አዝ
ደስ ላሰኝህ እቀናለሁ በሕይወቴ ላከብርህ
ሆኖም ከቶ አልጠቀምኩህም ሁሌ ሳሳዝንህ
ይልቅ ብዙ አድክሜሃለሁ የትም እየቀረሁ
ብዙም ስላላፈራሁ ኢየሱስ ከፍቶኝ አለቅሳለሁ

አዝ
ምን ያህል እንደሆነ አላውቅም ለክቼም አላየሁም
ግን አንድ ነገር አውቃለሁ
ስለወደድከኝ ወድሃለሁ (፪x)