እግዚአብሔር ፡ ሲረዳ (Egziabhier Sireda) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በሕይወት ፡ ጐዳና ፡ ፈተና ፡ ቢበዛም
ጌታን ፡ እየጠራ ፡ ንጹህ ፡ ሰው ፡ አይጠፋም
እጄን ፡ ያዘኝ ፡ ብሎ ፡ ሲጮህ ፡ ይሰማዋል
ከረግረግ ፡ አውጥቶ ፡ በድል ፡ ይመራዋል

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሲረዳ ፡ ከሰማያት ፡ ወርዶ
በደልን ፡ ሲያስወግድ ፡ በቅንነት ፡ ፈርዶ
አላያችሁም ፡ ወይ ፡ መጥመዱ ፡ ሲሰበር
ምርኮኛው ፡ ተለቆ ፡ ማዳኑን ፡ ሲናገር

ችግረኛውን ፡ ሊውጥ ፡ ጠላት ፡ ሲገዳደር
በሚያስፈራራ ፡ ቃል ፡ በትዕቢት ፡ ሲናገር
ደርሶ ፡ የሚታደግ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው
በሰው ፡ መታመን ፡ ግን ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ነው

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሲረዳ ፡ ከሰማያት ፡ ወርዶ
በደልን ፡ ሲያስወግድ ፡ በቅንነት ፡ ፈርዶ
አላያችሁም ፡ ወይ ፡ መጥመዱ ፡ ሲሰበር
ምርኮኛው ፡ ተለቆ ፡ ማዳኑን ፡ ሲናገር

ያለውን ፡ ተነጥቆ ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ አጥቶ
በአጠገቡ ፡ የሚቆም ፡ ጌታው ፡ ብቻ ፡ ቀርቶ
በእንግድነት ፡ አገር ፡ ተገርፎ ፡ ለሚያልፈው
ተስፋው ፡ መሰረቱ ፡ አምላኩ ፡ ብቻ ፡ ነው

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሲረዳ ፡ ከሰማያት ፡ ወርዶ
በደልን ፡ ሲያስወግድ ፡ በቅንነት ፡ ፈርዶ
አላያችሁም ፡ ወይ ፡ መጥመዱ ፡ ሲሰበር
ምርኮኛው ፡ ተለቆ ፡ ማዳኑን ፡ ሲናገር

የቅዱሳን ፡ ረድኤት ፡ ከሰማይ ፡ ይመጣል
ዘመናትን ፡ ቆጥሮ ፡ ጌታ ፡ ይመለሳል
የልጆቹን ፡ እንባ ፡ ከዓይናቸው ፡ ያብሳል
ክብርና ፡ ምሥጋና ፡ ለሥሙ ፡ ይሆናል

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሲረዳ ፡ ከሰማያት ፡ ወርዶ
በደልን ፡ ሲያስወግድ ፡ በቅንነት ፡ ፈርዶ
አላያችሁም ፡ ወይ ፡ መጥመዱ ፡ ሲሰበር
ምርኮኛው ፡ ተለቆ ፡ ማዳኑን ፡ ሲናገር


Navigation menu