እኛ ፡ ግን ፡ የሞተልንን (Egna Gen Yemotelenen) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አይሁድ ፡ ምልክት ፡ ይለምናሉ
ግሪኮች ፡ ጥበብ ፡ ይሻሉ
ጌታን ፡ ጥለው፡ ይቅበዘበዛሉ

አዝ፦ እኛ ፡ ግን ፡ የሞተልንን
በደሙም ፡ የተቤዥንን
አዳኝነቱን ፡ ንጉሥነቱን
ለፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እንሰብካለን
አዎን ፡ እንሰብካለን (፪x)

ያልገባቸው ፡ ያላወቁት ፡ በድንቅ
እንደ ፡ ሞኝነት ፡ ቢቆጥሩትም
በመስቀሉ ፡ ቃል ፡ አናፍርበትም

አዝ፦ እኛ ፡ ግን ፡ የሞተልንን
በደሙም ፡ የተቤዥንን
አዳኝነቱን ፡ ንጉሥነቱን
ለፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እንሰብካለን
አዎን ፡ እንሰብካለን (፪x)

የመዳኑን ፡ ፀጋ ፡ መጠራቱን
ከኃጢአን ፡ መሃል ፡ መውጣቱን
ባይቀበሉትም ፡ እንኳን ፡ ወንጌሉን

አዝ፦ እኛ ፡ ግን ፡ የሞተልንን
በደሙም ፡ የተቤዥንን
አዳኝነቱን ፡ ንጉሥነቱን
ለፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እንሰብካለን
አዎን ፡ እንሰብካለን (፪x)

ለእኛ ፡ ነህ ፡ መከታችን ፡ ኢየሱስ
ከለላችንም ፡ ክርስቶስ
አለቃችንም ፡ ነው ፡ የሰላም ፡ ንጉሥ

አዝ፦ እኛ ፡ ግን ፡ የሞተልንን
በደሙም ፡ የተቤዥንን
አዳኝነቱን ፡ ንጉሥነቱን
ለፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እንሰብካለን
አዎን ፡ እንሰብካለን (፪x)

ባዶ ፡ ተስፋ ፡ ፍፁም ፡ አናወራም
ከሥጋችን ፡ አንዘራም
ጌታችን ፡ አለና ፡ አንፈራም

አዝ፦ እኛ ፡ ግን ፡ የሞተልንን
በደሙም ፡ የተቤዥንን
አዳኝነቱን ፡ ንጉሥነቱን
ለፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እንሰብካለን
አዎን ፡ እንሰብካለን (፪x)

ለሚጠይቀን ፡ ሁሉ ፡ መልሳችን
የቀራንዮ ፡ ወዳጃችን
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ትምክህታችን


Navigation menu