ድል ፡ ለማድረግ ፡ ወጣ (Del Lemadreg Weta) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የፈርዖን ፡ ገንዘብ ፡ ያልማረከው ፡ ጀግና
ዓይኑ ፡ ያልደከመ ፡ ያላለቀ ፡ ገና
ድል ፡ ለማድረግ ፡ ወጣ ፡ በጦርነት ፡ ሲቃ
በጀርባው ፡ አንግቦ ፡ የአምላኩን ፡ ጦር ፡ ዕቃ (፪x)

የወይኒው ፡ አስራት ፡ የግርፋት ፡ ብዛት
አልቻለው ፡ ሊያበርደው ፡ የፍቅሩን ፡ ትኩሳት
ፎከረ ፡ ያ ፡ ጐበዝ ፡ ሊጥል ፡ ሊገረስስ
ጠምዶ ፡ በቀኝ ፡ እጁ ፡ የቃሉን ፡ መትረየስ (፪x)

ገና ፡ ዓይኑ ፡ ፍጦ ፡ ትኩር ፡ ብሎ ፡ እያየ
የጠላትን ፡ ምሽግ ፡ ቅጥሩን ፡ አጋዬ
የአርያም ፡ እሳት ፡ በኃይል ፡ ጐብኝቶታል
እባቡና ፡ ጊንጡን ፡ ከእግሩ ፡ ስር ፡ ረግጦታል (፪x)

በድካም ፡ በረታ ፡ ጅማቱ ፡ ጠንክሯል
አንገብግቦት ፡ ፍቅሩ ፡ ወኔው ፡ ተቀስቅሷል
በጀርባው ፡ መተልተል ፡ ጌታን ፡ አከበረ
የሞትንም ፡ ባሕር ፡ በእምነት ፡ ተሻገረ (፪x)


Navigation menu