በአምላክ ፡ አምሳል (Bamlak Amsal) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በአምላክ ፡ አምሳል ፡ ተፈጥሬ ፡ በጐ ፡ ለማድረግ ፡ በፊቱ
ስኖር ፡ ሳለሁ ፡ ኃጥያቴ ፡ አድርጐኝ ፡ ነበር ፡ ከንቱ
ክቡር ፡ ሆኜ ፡ ሳለሁ ፡ አምላኬን ፡ ረስቼ
እንደሚጠፉ ፡ እንስሶች ፡ መሰልኩ

እኔ ፡ ሳልፈልገው ፡ ጌታ ፡ ሊፈልገኝ ፡ ከላይ ፡ መጥቶ
ከእርኩሰት ፡ ውስጥ ፡ ነጥቆ ፡ አወጣኝ ፡ በዓለም ፡ ላይ ፡ ተንከራቶ
ሸክሜን ፡ ወሰደልኝ ፡ በሥጋዬ ፡ ሞተልኝ
የማይቆጠረውን ፡ በደሌን ፡ ፋቀልኝ

መድኃኒቴ ፡ ነው ፡ ኢየሱሴ ፡ ጌታዬና ፡ አምላኬ
ስለ ፡ መልካሙ ፡ ውለታው ፡ ላመስግነው ፡ ተንበርክኬ
ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ማዳኑ ፡ ግሩም ፡ ነው
ለአምላካዊ ፡ ፍቅሩ ፡ መጨረሻ ፡ የለው

በሞት ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ እያለሁ ፡ በድቅድቅ ፡ ጨለማ
ኢየሱስ ፡ ብርሃኔ ፡ መጥቶ ፡ አዳነኝ ፡ መሀሪ ፡ ነውና
ለፍርድ ፡ የተመደብኩ ፡ ለሲዖል ፡ የታጨሁ
የቁጣ ፡ ልጅ ፡ ስሆን ፡ ከፍጥረቴ
ቅጣቴን ፡ ውስዶ ፡ ያ ፡ ረድኤቴ (፪x)


Navigation menu