የማይናወጥ ፡ መሰረቴ (Yemayenawet Meseretie) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ የማይናወጥ ፡ መሠረቴ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መከታዬ
የህመሜ ፡ ፈውስ ፡ አሜን

በዚያ ፡ ሸለቆ ፡ በአዘንቱ ፡ ቦታ
ኢየሱስ ፡ አልተውከኝም ፡ ደጋፊ ፡ እንዳላጣ
ሕይወቴ ፡ ነህና ፡ ተድላ ፡ መከታዬ
ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ በቀር ፡ የቱ ፡ ነው ፡ ጋሻዬ

አዝ፦ የማይናወጥ ፡ መሠረቴ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መከታዬ
የህመሜ ፡ ፈውስ ፡ አሜን

የዓለሙ ፡ ወጀብ ፡ ሊመታኝ ፡ ሲቃጣ
ጌታ ፡ አለቀቀኝም ፡ ከእጁ ፡ እንድወጣ
ወደ ፡ እርሱ ፡ የመጡትን ፡ ልጆቹን ፡ ያፈቅራል
በእቅፍ ፡ ውስጥ ፡ ይዞ ፡ ይጠብቃቸዋል

አዝ፦ የማይናወጥ ፡ መሠረቴ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መከታዬ
የህመሜ ፡ ፈውስ ፡ አሜን

የጣርህን ፡ መጠን ፡ በምን ፡ ልገምተው
የውለታህን ፡ ልክ ፡ በምን ፡ ላስተውለው
ከቶ ፡ እንዳልዘነጋው ፡ ያንን ፡ መስቀልህን
ደግሞም ፡ እንዳልረሳ ፡ ለእኔ ፡ ማንባትህን

አዝ፦ የማይናወጥ ፡ መሠረቴ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መከታዬ
የህመሜ ፡ ፈውስ ፡ አሜን


Navigation menu