የባዘነውን ፡ ፈላጊ ፡ አምላክ (Yebazenewen Felagi Amlak) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(1)

እግዚአብሔር ፡ ኃያል
(Egziabhier Hayal)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

የጠራውን ፡ መስሎ ፡ መኖር ፡ መጋደሉን ፡ ፈርቶ
የገባለትን ፡ ቃልና ፡ ተስፋውን ፡ ዘንግቶ
የሙት ፡ ልጅ ፡ የነበረ ፡ ሰው ፡ ከጥፋት ፡ የዳነ
የተሰዋለትን ፡ ኢየሱስ ፡ ያንን ፡ አዳኙን ፡ ከዳ

አዝ፦ የባዘነውን ፡ ፋላጊ ፡ አምላክ
የምህረት ፡ አምባ ፡ ለጠፉትም ፡ የምታነባ
ከሕይወት ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ከእረፍት ፡ ወደ ፡ ጭንቀት
የሄደውን ፡ መልስ ፡ እባክህ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ መንጋህ ፡ በረት

ተዋግቶ ፡ የማረከውን ፡ ያንን ፡ ስመ ፡ ጥሩ ፡ ጀግና
ጌታውን ፡ ሊያስከብር ፡ ቆርጦ ፡ ተሰልፏልና
ጠላት ፡ ከባሻገር ፡ ቆሞ ፡ ቅናት ፡ እያጋየው
እሸክላውን ፡ ዘርግቶበት ፡ ወንድሜን ፡ ዘለፈው

አዝ፦ የባዘነውን ፡ ፋላጊ ፡ አምላክ
የምህረት ፡ አምባ ፡ ለጠፉትም ፡ የምታነባ
ከሕይወት ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ከእረፍት ፡ ወደ ፡ ጭንቀት
የሄደውን ፡ መልስ ፡ እባክህ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ መንጋህ ፡ በረት

በአምላኩ ፡ መቅደስ ፡ ውስጥ ፡ ሆኖ ፡ ተማምኖ ፡ እያገሳ
ገናናነቱንም ፡ ሲያውጅ ፡ የይሁዳን ፡ አንበሳ
እንግዳ ፡ ነገር ፡ ወሰደው ፡ ነዝንዞ ፡ ጨቅጭቆ
ፀጋ ፡ ክብሩን ፡ አስላጭቶ ፡ እጅግ ፡ አስጨንቆ

አዝ፦ የባዘነውን ፡ ፋላጊ ፡ አምላክ
የምህረት ፡ አምባ ፡ ለጠፉትም ፡ የምታነባ
ከሕይወት ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ከእረፍት ፡ ወደ ፡ ጭንቀት
የሄደውን ፡ መልስ ፡ እባክህ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ መንጋህ ፡ በረት

ጥቃቅኑ ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ጉልበቱን ፡ ከርክሮ
ጤናውን ፡ እየሰቀረበት ፡ በህመም ፡ አደንዝዞ
ያ ፡ የክህደት ፡ አውሎ ፡ በሕይወቱ ፡ ነፍሶበት
ከወይኑ ፡ ግንድ ፡ ገነጠለው ፡ ፍሬ ፡ እንዳይገኝበት

አዝ፦ የባዘነውን ፡ ፈላጊ ፡ አምላክ
የምህረት ፡ አምባ ፡ ለጠፉትም ፡ የምታነባ
ከሕይወት ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ከእረፍት ፡ ወደ ፡ ጭንቀት
የሄደውን ፡ መልስ ፡ እባክህ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ መንጋህ ፡ በረት