ኃጥያት ፡ ሥሩን ፡ ሰዶ (Hatiyat Serun Sedo) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ኃጢአት ፡ ሥሩን ፡ ሰዶ ፡ ሳይጠነክርብኝ
ሳይታወቀኝ ፡ አድጐ ፡ ሞትን ፡ ሳይወልድብኝ
ንስሃ ፡ እንደገባ ፡ በጊዜ ፡ ገስፀኝ (፪x)

የሌብነት ፡ ካባ ፡ ወርቁም ፡ ሆነ ፡ ብሩ
ከድንኳኔ ፡ በታች ፡ ተቀብረው ፡ ሳይቀሩ
ቃልህን ፡ ለመጠበቅ ፡ ልጆችህ ፡ ሲጥሩ
በተደበቀ ፡ እርም ፡ ወድቀው ፡ ሲማረሩ

አዝ፦ ኃጢአት ፡ ሥሩን ፡ ሰዶ ፡ ሳይጠነክርብኝ
ሳይታወቀኝ ፡ አድጐ ፡ ሞትን ፡ ሳይወልድብኝ
ንስሃ ፡ እንደገባ ፡ በጊዜ ፡ ገስፀኝ (፪x)

ኃጢአትን ፡ ታግፌ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ብልህም
ውስጤ ፡ ሳይስተካከል ፡ ብዘምርልህም
ወይም ፡ ብሰብክልህ ፡ ጉድለቴን ፡ ሳላውቀው
ምን ፡ ፍሬ ፡ ይገኛል ፡ በከንቱ ፡ መሮጥ ፡ ነው

አዝ፦ ኃጢአት ፡ ሥሩን ፡ ሰዶ ፡ ሳይጠነክርብኝ
ሳይታወቀኝ ፡ አድጐ ፡ ሞትን ፡ ሳይወልድብኝ
ንስሃ ፡ እንደገባ ፡ በጊዜ ፡ ገስፀኝ (፪x)

ጌታ ፡ ሆይ ፡ የለኝም ፡ ከአንተ ፡ የምቀርበው
ድካሜን ፡ ብርታቴን ፡ ተረድቶ ፡ የሚያውቅልኝ
ስለዚህ ፡ መርምረህ ፡ ንገረኝ ፡ በደሌን
ንስሃ ፡ ልግባ ፡ እኔ ፡ አዋርጄ ፡ እራሴን

አዝ፦ ኃጢአት ፡ ሥሩን ፡ ሰዶ ፡ ሳይጠነክርብኝ
ሳይታወቀኝ ፡ አድጐ ፡ ሞትን ፡ ሳይወልድብኝ
ንስሃ ፡ እንደገባ ፡ በጊዜ ፡ ገስፀኝ (፪x)


Navigation menu