እንባዬን ፡ አይተህ ፡ ጌታ (Enbayien Ayteh Gieta) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አንድን ፡ ነገር ፡ ሽቼ ፡ ደጅ ፡ ጠናለሁኝ
በቃልህ ፡ ከሆነ ፡ በዓይንህ ፡ ተመልከተኝ
ያቺን ፡ ብሩክ ፡ እጅህን ፡ ዘርጋብኝ

አዝ፦ እንባዬን ፡ አይተህ ፡ ጌታ
ለቅሶዬን ፡ ሰምተህ ፡ ጌታ
መሻቴን ፡ ስጠኝና ፡ ኢየሱስ ፡ ላመስግንህ (፪x)

አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጌ ፡ በቃልህ ፡ ፀንቼ
መልሴን ፡ አጠብቃለሁ ፡ በተመስጦ ፡ ሆኜ
ታማኝነትህን ፡ ተማምኜ

አዝ፦ እንባዬን ፡ አይተህ ፡ ጌታ
ለቅሶዬን ፡ ሰምተህ ፡ ጌታ
መሻቴን ፡ ስጠኝና ፡ ኢየሱስ ፡ ላመስግንህ (፪x)

በጐ ፡ ስጦታና ፡ ፍፁም ፡ በረከት ፡ ሁሉ
ከብርሃናት ፡ አባት ፡ ከላይ ፡ ይወርዳሉ
ከዙፋንህ ፡ ይንቆረቆራሉ

አዝ፦ እንባዬን ፡ አይተህ ፡ ጌታ
ለቅሶዬን ፡ ሰምተህ ፡ ጌታ
መሻቴን ፡ ስጠኝና ፡ ኢየሱስ ፡ ላመስግንህ (፪x)

መራራነቴ ፡ ያብቃ ፡ እሾህነቴም ፡ ያብቃ
መፈራረሴም ፡ ያብቃ ፡ በአንተ ፡ ፀጋ ፡ ልገንባ
ጐስቋላነቴን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እንካ

አዝ፦ እንባዬን ፡ አይተህ ፡ ጌታ
ለቅሶዬን ፡ ሰምተህ ፡ ጌታ
መሻቴን ፡ ስጠኝና ፡ ኢየሱስ ፡ ላመስግንህ (፪x)


Navigation menu