መነቀፍን ፡ ፈርቶ (Meneqefen Ferto) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ መነቀፍን ፡ ፈርቶ ፡ ማመን ፡ አፍሮ
ውድ ፡ አምላኩን ፡ ትቶ ፡ ቃልኪዳኑን ፡ ሰብሮ
ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ስንቱ ፡ ሰመጠ ፡ ባሕር ፡ ገብቶ
ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ድረስ ፡ እርዳን ፡ ብሎ ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ተጸጽቶ

በመንፈስ ፡ ጀምሮ ፡ ሮጦ ፡ ሮጦ
ከዓለም ፡ ማዕረግ ፡ መቀመጥ ፡ መርጦ
ዛሬ ፡ ግን ፡ በወሬ ፡ ልቡ ፡ ቀልጦ
መመካከር ፡ ያለ ፡ ጠላት ፡ መርጦ

አዝ፦ መነቀፍን ፡ ፈርቶ ፡ ማመን ፡ አፍሮ
ውድ ፡ አምላኩን ፡ ትቶ ፡ ቃልኪዳኑን ፡ ሰብሮ
ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ስንቱ ፡ ሰመጠ ፡ ባሕር ፡ ገብቶ
ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ድረስ ፡ እርዳን ፡ ብሎ ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ተጸጽቶ

እርግማን ፡ አይደለም ፡ መቃረኑ
መነቀፍ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ አስተውሎ
ከአሁኑ ፡ ዓለም ፡ ተወዳጅቶ
ክርስቶስን ፡ መተው ፡ ይቅር ፡ ከቶ

አዝ፦ መነቀፍን ፡ ፈርቶ ፡ ማመን ፡ አፍሮ
ውድ ፡ አምላኩን ፡ ትቶ ፡ ቃልኪዳኑን ፡ ሰብሮ
ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ስንቱ ፡ ሰመጠ ፡ ባሕር ፡ ገብቶ
ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ድረስ ፡ እርዳን ፡ ብሎ ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ተጸጽቶ

መስቀሉን ፡ ከጫንቃቸው ፡ ለጣሉ
እኛም ፡ ክርስቲያኖች ፡ ነን ፡ ለሚሉ
ይለፍ ፡ ለሌላቸው ፡ መንገደኞች
እንጸልይላቸው ፡ ለኮብላዮች

አዝ፦ መነቀፍን ፡ ፈርቶ ፡ ማመን ፡ አፍሮ
ውድ ፡ አምላኩን ፡ ትቶ ፡ ቃልኪዳኑን ፡ ሰብሮ
ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ስንቱ ፡ ሰመጠ ፡ ባሕር ፡ ገብቶ
ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ድረስ ፡ እርዳን ፡ ብሎ ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ተጸጽቶ

መስቀሉን ፡ ቢረዳ ፡ ዓይኑ ፡ በርቶ
ንስሃ ፡ ቢገባ ፡ ዳግም ፡ ቀንቶ
እጅህ ፡ መቼ ፡ አጠረች ፡ የማዳንህ
ከጥልቁ ፡ ቢጣራ ፡ ይልቁን ፡ ልጅህ

አዝ፦ መነቀፍን ፡ ፈርቶ ፡ ማመን ፡ አፍሮ
ውድ ፡ አምላኩን ፡ ትቶ ፡ ቃልኪዳኑን ፡ ሰብሮ
ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ስንቱ ፡ ሰመጠ ፡ ባሕር ፡ ገብቶ
ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ድረስ ፡ እርዳን ፡ ብሎ ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ተጸጽቶ


Navigation menu