ኢየሱስ (Eyesus) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ የሰላሙ ፡ ንጉሥ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ና ፡ ሕይወቴን ፡ ፈውስ

ወደ ፡ እኔ ፡ ጩህ ፡ እኔም ፡ እመልሳለሁ
ታላቁንም ፡ ነገር ፡ ለአንተ ፡ አሳይሃለሁ
በቃልህ ፡ ስላልከኝ ፡ እንዲህ ፡ እጮሃለሁ
እንድትፈውሰኝ ፡ ሥምህን ፡ ጠራለሁ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ የሰላሙ ፡ ንጉሥ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ና ፡ ሕይወቴን ፡ ፈውስ

በድካም ፡ ማዕበል ፡ ሕይወቴ ፡ ተከፍቶ
በሚሰብር ፡ በትር ፡ ክፉኛ ፡ ተመቶ
የታመቀው ፡ ስቃይ ፡ ልብን ፡ እየጣሰ
እንባን ፡ አስክትሎ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ደረሰ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ የሰላሙ ፡ ንጉሥ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ና ፡ ሕይወቴን ፡ ፈውስ

አልጥልህም ፡ ብለህ ፡ ከቶም ፡ አለቅህም
የገባህልኝ ፡ ቃል ፡ አልተዘነጋኝም
እኔ ፡ ፈዋሽህ ፡ ነኝ ፡ ብለህ ፡ የፈወስከኝ
ከጉስቁልናዬ ፡ ና ፡ ዛሬም ፡ አድነኝ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ የሰላሙ ፡ ንጉሥ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ና ፡ ሕይወቴን ፡ ፈውስ

ሰባራውን ፡ ጠጋኝ ፡ የፈረሰውን ፡ አዳሽ
ፈዋሽ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የእንባዬ ፡ አባሽ
ሰዎች ፡ ያላዩትን ፡ ቁስሌን ፡ ያየህልኝ
አንተ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህልኝ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ የሰላሙ ፡ ንጉሥ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ና ፡ ሕይወቴን ፡ ፈውስ

Navigation menu