እስከዛሬ ፡ ደረስ (Eskezarie Deres) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ እስከዛሬ ፡ የጠበከን
ከፍላጻ ፡ የሸፈንከን
ዳርቻችንንም ፡ ያሰፋህልን
እንባችንን ፡ ና ፡ አብስልን

በማይገለጸው ፡ ክብርህ
በማይካድ ፡ ጉልበትህ
አንድነትን ፡ አሳየን
ለእኛም ፡ ከለላ ፡ የሆንህ

አዝ፦ እስከዛሬ ፡ የጠበከን
ከፍላጻ ፡ የሸፈንከን
ዳርቻችንንም ፡ ያሰፋህልን
እንባችንን ፡ ና ፡ አብስልን

የጠላትን ፡ ቁጣ ፡ አይተን
ልካችንን ፡ ስንመስል
ተስፋ ፡ ቆርጠን ፡ ወየው ፡ ስንል
አማኑኤል ፡ ደረስክልን

አዝ፦ እስከዛሬ ፡ የጠበከን
ከፍላጻ ፡ የሸፈንከን
ዳርቻችንንም ፡ ያሰፋህልን
እንባችንን ፡ ና ፡ አብስልን

በማባበል ፡ ሊያስማማን
ካልተሳካው ፡ ሊያስፈራራን
ጠላት ፡ ሲዝት ፡ ሲያሽካካብን
ሴራውን ፡ ያከሸፍክልን

አዝ፦ እስከዛሬ ፡ የጠበከን
ከፍላጻ ፡ የሸፈንከን
ዳርቻችንንም ፡ ያሰፋህልን
እንባችንን ፡ ና ፡ አብስልን

ድብልቅ ፡ ኑሮ ፡ ያልኖረ
ከእግዚአብሔርም ፡ የተማረ
ቢማቅቅም ፡ ያሸንፋል
የአምላኩንም ፡ ሥም ፡ ያስጠራል

አዝ፦ እስከዛሬ ፡ የጠበከን
ከፍላጻ ፡ የሸፈንከን
ዳርቻችንንም ፡ ያሰፋህልን
እንባችንን ፡ ና ፡ አብስልን


Navigation menu