ሳልወድህ ፡ የወደድከኝ (Salwedeh Yewededkegn) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሳልወድህ ፡ የወደድከኝ ፡ ሳልመርጥህ ፡ የመረጥከኝ
በከበረው ፡ ደም ፡ ገዝተህ ፡ እንዲያው ፡ ልጅህ ፡ ያረከኝ
አበሳዬን ፡ አራከው ፡ ቀንበሬን ፡ ሰባበርከው
(ፍቅርህ ፡ ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ስምህን ፡ ላሞጋግሰው) (፪x)

ኃጢአተኛ ፡ሳለሁ ፡ ጽድቅ ፡ የማይገባኝ
መርገሜን ፡ ወሰደው ፡ ኢየሱስ ፡ በደሙ ፡ አነጻኝ
የከሰሰኝ ፡ ጠላት ፡ እግሬ ፡ ስር ፡ ወደቀ
በረሃው ፡ ሕይወቴ ፡ ምንጭን ፡ አፈለቀ

ለዚህ ፡ የሚያበቃ ፡ ጽድቅ ፡ እንኳን ፡ ሳይኖረኝ
በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በቀኙ ፡እንዲሁ ፡ አከበረኝ
ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ይሄ ፡ ታላቅ ፡ ጌታ
ከእኔ ፡ ጋር ፡ ሆናችሁ ፡ በዜማ ፡ አክብሩት ፡ በልልታ

አዝ
ሳልወድህ ፡ የወደድከኝ

የዕዳ ፡ ጽህፈቴን ፡ በደሙ ፡ ደምስሶ
ጠላቴን ፡ በእጄ ፡ እረግጦ ፡ ሰጠኝ ፡ አሳልፎ
ጽኑ ፡ ስልጣን ፡ አለኝ ፡ የአምላክ ፡ ልጅ ፡ ሆኛለሁ
የፈታኝን ፡ ጌታ ፡ ተፈትቸ ፡ አከብረዋለሁ

አዝ
ሳልወድህ ፡ የወደድከኝ

ለዚህ ፡ የሚያበቃ ፡ ጽድቅ ፡ እንኳን ፡ ሳይኖረኝ
በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በቀኙ ፡እንዲሁ ፡ አከበረኝ
ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ይሄ ፡ ታላቅ ፡ ጌታ
ከእኔ ፡ ጋር ፡ ሆናችሁ ፡ በዜማ ፡ አክብሩት ፡ በልልታ

አዝ
ሳልወድህ ፡ የወደድከኝ

Navigation menu