Teodros Tadesse/Wa/Wa

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

| ዘማሪ=ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ | | የመሞቴን ዜና ሊሰማ

  እንደቋመጠ ልክ እንደሃማ 
  እግዚአብሔር ሲፈርድልኝ ለኔ 
  እንደመርዶኪዎስ ሆነ ዘመኔ
    ምህረቱ ነው የከለለኝ
    ቸርነቱ  የደገፈኝ
    አጥፊዎች እያሉ በሕይወት መኖሬ
    ጥበቃው በዝቶ እንጂ እኔስ እስከዛሬ
  ምህረቱ ነው የከለለኝ
  ቸርነቱ  የደገፈኝ
  ነገር ተገልብጦ የከሳሼ ወሬ
  ውርደቴ ሲጠበቅ ተሰማ መክበሬ
  ምህረቱ ነው የከለለኝ
  ቸርነቱ  የደገፈኝ
   አምላኩን ተማምኖ ደጁ ላይ 
   ሆኖ ለታገሰው ሰው
   እንዲህ ይደረጋል ንጉስ ለወደደው  
    ደግሞም ላከበረው
    የጠላትን ምክር ከንቱ አርድጎልኝ 
     የሰራውን ሴራ 
   ለክፉ ያሰበው ለመልካም ሆነልኝ
    ደርሶ የኔ ተራ
    በንጉስ ፈረስ ላይ ተቀምጦ/2 
    እድፋሙ ልብሱ ተለውጦ/2
    መለከት ይነፋ ይታወጅ አዋጅ
   መስቀል ላይ ሟች ነበርኩ ቀይሮልኝ እንጂ
    በፊቱ መውድቅ የጀመርክለት 
    አይሁድ ከሆነ ኪዳን ያለበት
     ትነካውና ዋ!
     የተባለልኝ ለእኔ ነዋ
 
    ስታመነው አየኝ ስደገፈው አየኝ
    ፍርዱ ለተዛባ እኔ አለሁለት አለኝ
    የመሞቴን ዜና ሊሰማ 
    እንደቋመጠ ልክ እንደሃማ 
   እግዚአብሔር ሲፈርድልኝ ለኔ 
   እንደመርዶኪዎስ ሆነ ዘመኔ
    ምህረቱ ነው የከለለኝ
    ቸርነቱ ነው የደገፈኝ
    አጥፊዎች እያሉ በሕይወት መኖሬ
    ጥበቃው በዝቶ እንጂ እኔስ እስከዛሬ
     ምህረቱ ነው የከለለኝ
  ቸርነቱ ነው የደገፈኝ
  ነገር ተገልብጦ የከሳሼ ወሬ
  ውርደቴ ሲጠበቅ ተሰማ መክበሬ
  ምህረቱ ነው የከለለኝ
  ቸርነቱ  የደገፈኝ
  አዋጅ ሲፈራረቅ ያለመናወጥ ፀንቶ የጠበቀ 
  ብድራቱን አይቶ ያላመቻመቸ ስፍራ ያልለቀቀ
  የኋላ የኋላ ውርደቱን በክብር ሀዘኑን በደስታ
 ለውጦክ ሶታል ሊከፍለው ሲመጣ ያከበረው
   ጌታ
  በንጉስ ፈረስ ላይ ተቀምጦ 
  እድፋሙ ልብሱ ተለውጦ
  መለከት ይነፋ ይታወጅ አዋጅ
  መስቀል ላይ ሟች ነበርኩ ቀይሮልኝ እንጂ
   በፊቱ መውድቅ የጀመርክለት 
   አይሁድ ከሆነ ኪዳን ያለበት
   ትነካትና ዋ!
   የተባለልኝ ለእኔ ነዋ
   ስታመነው አየኝ ስደገፈው አየኝ
   ፍርዱ ለተዛባ እኔ አለሁለት አለኝ
   እኔ አለሁለት አለኝ
   አለሁልህ አለኝ