ወረደልኝ (Weredelegn) - ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Teodros Tadesse)

Teodros Tadesse 1.jpeg


(1)

አያምረኝም
(Ayamregnm)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Teodros Tadesse)

 
ተስፋዬ????????

የኋላዬን ፡ እየረሳሁ ፡ የፊቴን ፡ ለመያዝ ፡ እዘረጋለሁ
ወዳየሁት ፡ መድረሻዬ ፡ ውጊያው/ሰልፉ ፡ ቢበረታም ፡ ሄጄ ፡ እወርሳለሁ (፪x)

እንዴት ፡ ይሆናል ፡ አልልም ፡ ሆኖ ፡ ስለማየው
ተስፋ ፡ የሰጠው ፡ በእርግጥም ፡ እርሱ ፡ የታመነ ፡ ነው (፬x)

ህልመኛው ፡ ህልሙ ፡ ሳይፈታ ፡ ከግዞት ፡ ወርዶ ፡ ቢገላተል???
ቅዠት ፡ አይደለም ፡ እውን ፡ ነዉ ፡ ማለፊያው ፡ መውጪያው ፡ ጭንቅ ፡ ነዉ
ይሁን ፡ እንጂ ፡ ጌታውን ፡ የጠበቀ ፡ አይቀርምና ፡ መክበሩ
ቆይቶ ፡ ደጅ ፡ ለጠና ፡ ዘምበል ፡ ላለለት ፡ በክብሩ

ብዬ ፡ ተቀኘሁኝ ፡ እንደገና (እንደገና)
የጌታዬን ፡ ማዳን ፡ አየሁና
ብዬ ፡ ተቀኘሁኝ ፡ እንደገና (እንደገና)
የአለፈውን ፡ ሕይወቴን ፡ አሰብኩና
ወረደልኝ ፣ ፈረደልኝ ፣ ደረሰልኝ ፣ አሻገረኝ (፪x)
ከላዬ ፡ ከላዬ ፡ ሰላሜ ፡ ሰላሜ (፪x)
ከላዬ(፬x)

የኋላዬን (የኋላዬን) ፡ እየረሳሁ (እየረሳሁ) ፡ የፊቴን ፡ ለመያዝ ፡ እዘረጋለሁ
ወዳየሁት ፡ መድረሻዬ ፡ ውጊያው፡ ቢበረታም ፡ ሄጄ ፡ እወርሳለሁ (ካለው?? ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ)
የኋላዬን (አዎ) ፡ እየረሳሁ (እየረሳሁ) ፡ የፊቴን ፡ ለመያዝ ፡ እዘረጋለሁ (እዘረጋለሁ)
ወዳየሁት ፡ መድረሻዬ (መድረሻዬ) ፡ ሰልፉ፡ ቢበረታም ፡ ሄጄ ፡ እወርሳለሁ (ሄጄ ፡ እወርሳለሁ)

እንዴት ፡ ይሆናል ፡ አልልም ፡ ሆኖ ፡ ስለማየው
ተስፋ ፡ የሰጠው ፡ በእርግጥም ፡ እርሱ ፡ የታመነ ፡ ነው (፬x)

ምን ፡ ብትገፋ ፡ በጣውንቷ ፡ ነብይ ፡ ወለደኝ ፡ መካኒቷ
ጽዋው ፡ መራር ፡ ነው ፡ የመከራ ፡ ቀኑ ፡ እስኪደርስ ፡ በየተራ
ይሁን ፡ እንጂ ፡ ጌታውን ፡ የጠበቀ ፡ አይቀርምና ፡ መክበሩ
ቆይቶ ፡ ደጅ ፡ ለጠና ፡ ዘምበል ፡ ላለለት ፡ በክብሩ

ብዬ ፡ ተቀኘሁኝ ፡ እንደገና (እንደገና)
የጌታዬን ፡ ማዳን ፡ አየሁና
ብዬ ፡ ተቀኘሁኝ ፡ እንደገና (እንደገና)
የአለፈውን ፡ ሕይወቴን ፡ አሰብኩና
ወረደልኝ (ወረደልኝ) ፣ ፈረደልኝ (ፈረደልኝ)
ደረሰልኝ (ደረሰልኝ) ፣ አሻገረኝ (አሻገረኝ) (፪x)
ከላዬ (፰x)

Navigation menu