አምጡ (Amtu) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ነገሥታት ፡ ቢቀየሩ
(Negestat Biqeyeru)

ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

ገና ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና (፬x)

ገና ፡ ገና ፡ መቼ ፡ ይበቃውና (፪x)
ገና ፡ ገና ፡ ዛሬም ፡ እንደገና (፪x)
ገና ፡ ገና ፡ እሰዋለሁ ፡ ገና (፪x)

ገና ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና (፬x)

አልጠግብም ፡ ባመሰግነው ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ብለው
ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ያረገው ፡ ውለታው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
አልውልም ፡ ሳላነሳሳው ፡ ሥሙ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው
እንደገና ፡ አከብረዋለሁ ፡ ምሥጋናዬ ፡ እስኪ ፡ ይድረሰው

አዝ፦ አምጡ ፡ ምሥጋና ፡ አምጡ (፬x)
አምጡ ፡ ዝማሬ ፡ አምጡ (፬x)
አምጡ ፡ ዕልልታ ፡ አምጡ (፬x)
አምጡ ፡ ጭብጨባ ፡ አምጡ (፬x)
ጨምሩ ፡ ለጌታ ፡ ጨምሩ (፬x)
በተዋበ ፡ ዜማ ፡ ዘምሩ (፬x)

ሀያ ፡ አራት ፡ ሽማግሌዎች ፡ ወድቀው ፡ ክብርን ፡ ይሰጡሀል
መላዕክት ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ይገባሀል ፡ ለአንተ ፡ ይሉሀል
እኔም ፡ ባለችኝ ፡ ጊዜዬ ፡ ላክብርህ ፡ ውዱ ፡ ጌታዬ
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ እላለሁ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ባለውለታዬ

ገና ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና (፬x)
ገና ፡ ገና ፡ መቼ ፡ ይበቃውና (፪x)
ገና ፡ ገና ፡ ዛሬም ፡ እንደገና (፪x)
ገና ፡ ገና ፡ እሰዋለሁ ፡ ገና (፪x)

አዝ፦ አምጡ ፡ ምሥጋና ፡ አምጡ (፬x)
አምጡ ፡ ዝማሬ ፡ አምጡ (፬x)
አምጡ ፡ ዕልልታ ፡ አምጡ (፬x)
አምጡ ፡ ጭብጨባ ፡ አምጡ (፬x)
ጨምሩ ፡ ለጌታ ፡ ጨምሩ (፬x)
በተዋበ ፡ ዜማ ፡ ዘምሩ (፬x)