ጌታ ፡ ተመሥገን (Gieta Temesgen) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Lyrics.jpg


(2)

ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው
(Mekniyatie Bezu New)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

ክበርልኝ ፡ ብዬ ፡ ገና ፡ አልጠገብኩም
ንገሥልኝ ፡ ብዬ ፡ በልቤ ፡ አልረካሁም
ከምሥጋና ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ምትወደው
ባቀርብልህ ፡ ጌታ ፡ ከምንም ፡ ባልሰለቸሁ (፪x)

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ብለው ፡ ሁሌ ፡ ከሚያከብሩህ
እኔን ፡ ከመደብከኝ ፡ ከሚያመሰግኑህ
ጥማቴ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ እኔ ፡ አከብርሃለሁ
በቀንም ፡ በሌሊት ፡ ምሥጋና ፡ እሰዋለሁ

አዝ፦ ብቻ ፡ አንተ ፡ ከወደድከው
ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው (፪x)

ሰማይና ፡ ምድር ፡ ክብርን ፡ ያወራሉ
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እያሉ
እኔም ፡ በተራዬ ፡ ለትውልድ ፡ ልናገር
የሚመስልህ ፡ የለም ፡ ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ ክበር

አዝ፦ ብቻ ፡ አንተ ፡ ከወደድከው
ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው (፪x)

ፊትህን ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ መልሰሃልና
የአንተ ፡ ወገን ፡ አርገህ ፡ ዋጅተኸኛልና
ከምርጦችህ ፡ ጋራ ፡ እኔም ፡ ተስማምቼ
እሰግድልሃለሁ ፡ መቅደስህ ፡ ገብቼ

አዝ፦ ብቻ ፡ አንተ ፡ ከወደድከው
ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው (፪x)

የምለው ፡ ብዙ ፡ አለኝ ፡ ስላንተ ፡ ማወራው
አምላኬ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ የምናገረው
የሚሰማኝና ፡ የሚያየኝ ፡ ያክብርህ
የእኔ ፡ ብቻ ፡ አይበቃም ፡ ዘሬም ፡ ይገዛልህ

ክበርልኝ ፡ ብዬ ፡ ገና ፡ አልጠገብኩም
ንገሥልኝ ፡ ብዬ ፡ በልቤ ፡ አልረካሁም
ከምሥጋና ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ምትወደው
ባቀርብልህ ፡ ጌታ ፡ ከምንም ፡ ባልሰለቸሁ (፪x)

አዝ፦ ብቻ ፡ አንተ ፡ ከወደድከው
ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው (፬x)