Tekeste Getnet/Deg Neh/Lebie Tsena

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ልቤ ፡ ፀና
ልቤ ፡ በአንተ ፡ ፀና (፪x)

ቃልህን ፡ ይዣለሁ ፡ ባይታይ ፡ ደመና
ዘምር ፡ ዘምር ፡ አለኝ ፡ ልቤ ፡ በአንተ ፡ ፀና

አዝ፦ ልቤ ፡ ፀና

ልቤ ፡ በአንተ ፡ ፀና (፪x)


ሳይቀየር ፡ ሁሉ ፡ እንዳለ ፡ ሆኖ
ሲያመሰግን ፡ በአምላኩ ፡ ተማምኖ
ምድረበዳን ፡ የሚያለመልመው
በረሃውን ፡ ገነት ፡ አደረገው


ሳይቀየር ፡ ሁሉ ፡ እንዳለ ፡ ሆኖ
ሲያመሰግን ፡ በአምላኩ ፡ ተማምኖ
ምድረበዳን ፡ የሚያለመልመው
ድንገት ፡ ደርሶ ፡ ታሪኩን ፡ ቀየረ


አዝ፦ ልቤ ፡ ፀና

ልቤ ፡ በአንተ ፡ ፀና (፪x)


ቃልህን ፡ ይዣለሁ ፡ ፡ ባይታይ ፡ ደመና
ዘምር ፡ ዘምር ፡ አለኝ ፡ ልቤ ፡ በአንተ ፡ ፀና

አዝ፦ ልቤ ፡ ፀና

ልቤ ፡ በአንተ ፡ ፀና (፪x)


በገናዬ ፡ ከተሰቀለበት
ይውረድና ፡ ቅኔን ፡ ልቀኝበት
ሁኔታው ፡ ሳይቀያየር
አውቅበት ፡ የለ ፡ ለአንተ ፡ መዘምር

በገናዬ ፡ ከተሰቀለበት
ይውረድ ፡ እንጂ ፡ ቅኔን ፡ ልቀኝበት
ሁኔታው ፡ ሳይቀያየር
አውቅበት ፡ የለ ፡ ለአንተ ፡ መዘምር

ምሥጋና ፡ ለሥምህ
ምሥጋና ፡ ለክብርህ
ይገባሃል ፡ ጌታ
አይጓደለብህ


ዝማሬ ፡ ለሥምህ
ዝማሬ ፡ ለክብርህ
ይገባሃል ፡ አንተስ
አይጓደለብህ


ባያድነን ፡ እኛስ ፡ ለአንተ ፡ አንሰግድም
ላቆመውከው ፡ ምስል ፡ ፈፅሞ ፡ እጅ ፡ አንሰጥም
ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ቢነድም ፡ እሳቱ
ይመለካል ፡ የእኛስ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x)

ምሥጋና ፡ ለሥምህ
ምሥጋና ፡ ለክብርህ
ይገባሃል ፡ ጌታ
አይጓደለብህ


ዝማሬ ፡ ለሥምህ
ዝማሬ ፡ ለክብርህ
ይገባሃል ፡ አንተስ
አይጓደለብህ


ባሪያዎችህ ፡ ወህኒ ፡ ቤት ፡ ተጥለው
ግን ፡ ሲያመልኩ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ብለው
የወህኒውን ፡ መሠረት ፡ አናውጠህ