አባት ፡ አግኝቻለሁ (Abat Aggnechalehu) - ተፈራ ፡ ነጋሽ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ተፈራ ፡ ነጋሽ
(Tefera Negash)

Tefera Negash 1.jpg


(1)

አልመለስም
(Alemelesem)

ዓ.ም. (Year): 2011
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተፈራ ፡ ነጋሽ ፡ አልበሞች
(Albums by Tefera Negash)

 
ጠላቴ ፡ ያሻውን ፡ ቢያወራ ፡ አልሰማም ፡ እንኳንስ ፡ ልፈራ
አምላኬ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አድራለሁ ፡ አስተማማኝ ፡ ጋሻ ፡ አግኝቻለሁ
ዲያቢሎስ ፡ ቢፎክር ፡ ቢያወራ ፡ አልሰማም ፡ እንኳንስ ፡ ልፈራ
አምላኬ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አድራለሁ ፡ የሚያኮራ ፡ አባት ፡ አግኝቻለሁ

አዝ፦ አግኝቻለሁ ፡ አባት ፡ አግኝቻለሁ (፬x)

ደሙ ፡ በጉ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ ስላለ ፡ ጥፋት ፡ መቼም ፡ አያገኘኝ
እንደ ፡ ዐይኑ ፡ ብሌን ፡ ይጠብቀኛል ፡ እግዚአብሔር ፡ መቼም ፡ አይተወኝ
ያ ፡ የጨለማ ፡ ዘመን ፡ አለፈ ፡ አበቃ ፡ ብርሃን ፡ በራ
አሻገረኝ ፡ በበረታች ፡ ክንዱ ፡ ነፃ ፡ ወጣሁ ፡ በአምላክ ፡ ስራ

ፈርዖን ፡ ከኋላ ፡ ቀይ ፡ ባሕር ፡ ከፊቴ
ከብቦኝ ፡ ቢደነፋ ፡ ቢፎክር ፡ ጠላቴ
እግዚአብሔር ፡ ሲነሳ ፡ ጠላቶቼ ፡ ሁሉ ፡ በሰባት ፡ መንገድ ፡ ይበታተናሉ
ኃያሉ ፡ ሲነሳ ፡ የከበቡኝ ፡ ሁሉ ፡ በሰባት ፡ መንገድ ፡ ይበታተናሉ

ምድሩን ፡ ማዕበሉን ፡ አልፈራ ፡ እግዚአብሔር ፡ በኃይሉ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
በአምላኬ ፡ እተማመናለሁ ፡ ጠላቴ ፡ ይሰጥማል ፡ እኔ ፡ እሻገራለሁ

አዝ፦ አግኝቻለሁ ፡ አባት ፡ አግኝቻለሁ (፬x)

ማዕበል ፡ ወጀቡ ፡ ቢነሳ ፡ ተራራው ፡ ቢገተር ፡ ከፊቴ
ሁሉም ፡ ትክክል ፡ ይሆናል ፡ ትዕዛዝ ፡ ሲወጣ ፡ ከአባቴ
መድኃኒቴ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ አልፈራም ፡ እተማመናለሁ
እባቡን ፡ እና ፡ ዘንዶውን ፡ እረጋግጬው ፡ አልፋለሁ

ሰይጣን ፡ ተማምሎ ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ቢነሳ
ሊውጠኝ ፡ ቢጐመጅ ፡ ዙሪያዬን ፡ ቢያገሳ
ልቤ ፡ አይደነግጥም ፡ በከንቱ ፡ ፉከራ
እግዚአብሔር ፡ ጋሻዬ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ልቤ ፡ አይደነግጥም ፡ በከንቱ ፡ ፉከራ
እግዚአብሔር ፡ አባቴ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ

ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አምላክ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ጌታ ፡ ከኔ ፡ ጋራ

ፈርዖን ፡ ከኋላ ፡ ቀይ ፡ ባሕር ፡ ከፊቴ
ከብቦኝ ፡ ቢደነፋ ፡ ቢፎክር ፡ ጠላቴ
እግዚአብሔር ፡ ሲነሳ ፡ ጠላቶቼ ፡ ሁሉ ፡ በሰባት ፡ መንገድ ፡ ይበታተናሉ
ኃያሉ ፡ ሲነሳ ፡ የከበቡኝ ፡ ሁሉ ፡ በሰባት ፡ መንገድ ፡ ይበታተናሉ

ወጀቡን ፡ ማዕበሉን ፡ አልፈራ ፡ እግዚአብሔር ፡ በኃይሉ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
በአምላኬ ፡ እተማመናለሁ ፡ ጠላቴ ፡ ይሰጥማል ፡ እኔ ፡ እሻገራለሁ

አዝ፦ አግኝቻለሁ ፡ አባት ፡ አግኝቻለሁ (፰x)


Navigation menu