ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን (Gieta Hoy And Sew Seten) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ታምራት ፡ ኃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(8)

ኢየሱስ ፡ ነካኝ ፡ በድንገት
(Eyesus Nekagn Bedenget)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 6:56
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ኃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አዝጌታ ፡ ሆይ (፪x) ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን
የእግዚአብሔር ፡ ቅባት ፡ ያለበት
ቢባርክ ፡ የሚደርስለት ፡ ቢረግም ፡ የሚሆንለት
ቢገስፅ ፡ የምንሰማው ፡ ቢቆጣን ፡ የምንፈራው
ስንተኛ ፡ የሚያነቃን ፡ ስንሮጥ ፡ የሚያቆመን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን (፪x)

ፍቅርን ፡ ተቀብሎ ፡ የሚሰጥ ፡ የፍቅር ፡ መጋቢ
ሀብታም ፡ ደሀ ፡ ብርቱ ፡ ደካማ ፡ ሁሉንም ፡ ሰብሳቢ
በፍቅር ፡ በርህራሄ ፡ በትዕግስት ፡ መንጋህን ፡ ሚመራ
የቆሰለ ፡ ፈዋሽ ፡ መድኃኒት ፡ ደራሽ ፡ በመከራ

አዝጌታ ፡ ሆይ (፪x) ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን
የእግዚአብሔር ፡ ቅባት ፡ ያለበት
ቢረግምም ፡ የሚደርስለት ፡ ቢባርክ ፡ የሚሆንለት
ቢከፋን ፡ የምናዋየው ፡ ቢደክመን ፡ የምናርፍበት
ብንቆስል ፡ የሚፈውሰን ፡ ብናዝን ፡ የሚያፅናናን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን (፪x)

ጩኸት ፡ አብዝተናል ፡ ውድድር ፡ እኔ ፡ እበልጥ ፡ እኔ ፡ እበልጥ
ሁላችንም ፡ እኩል ፡ ሆነናል ፡ የለም ፡ መደማመጥ
እረፉ ፡ የሚለን ፡ ተቆጪ ፡ እንደምን ፡ እንጣ
ጌታሆይ ፡ እባክህ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ በቅባትህ ፡ አውጣ

አዝጌታ ፡ ሆይ (፪x) ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን
የእግዚአብሔር ፡ ቅባት ፡ ያለበት
ቢባርክ ፡ የሚደርስለት ፡ ቢረግምም ፡ የሚሆንለት
ስንበድል ፡ የሚገስፀን ፡ ስንስት ፡ የሚመልሰን
ስንጣላ ፡ የሚያስታርቀን ፡ ስንበተን ፡ ሚሰበስበን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን (፪x)

ቃሉ ፡ ከምድር ፡ ጠብ ፡ የማይል ፡ ቀንዱ ፡ ዘይት ፡ የሞላ
ለተገፉ ፡ ድሆች ፡ ተሟጋች ፡ ጉቦ ፡ የማይበላ
ለእውነት ፡ ኖሮ ፡ ለእውነት ፡ የሚሞት ፡ በዚህ ፡ ክፉ ፡ ዘመን
ነገስታት ፡ ሲያጠፉ ፡ ሀይ ፡ የሚል ፡ ሳሙኤልን ፡ ስጠን

አዝጌታ ፡ ሆይ (፪x) ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን
የእግዚአብሔር ፡ ቅባት ፡ ያለበት
ቢባርክ ፡ የሚደርስለት ፡ ቢረግምም ፡ የሚሆንለት
ስንፈራ ፡ ሚያደፋፍረን ፡ ስንጨነቅ ፡ አይዞ ፡ የሚለን
ስንገፋ ፡ ሚሟገትልን ፡ ስንናቅ ፡ የሚቆምልን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን (፪x)

ቅድስት ፡ ከተማ ፡ ቅጥሯ ፡ ፈርሶ ፡ መቅደሱ ፡ ሲቃጠል
በንጉስ ፡ ጮማ ፡ በወይን ፡ ጠጅ ፡ የማይቀማጠል
ህዝብህን ፡ የሚያነሳሳ ፡ ቅጥሩን ፡ ለመጠገን
ክብሩን ፡ ስለ ፡ ክብርህ ፡ የተወ ፡ ነህምያን ፡ ስጠን

አዝጌታ ፡ ሆይ (፪x) ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን
የእግዚአብሔር ፡ ቅባት ፡ ያለበት
ቢባርክ ፡ የሚደርስለት ፡ ቢረግምም ፡ የሚሆንለት
ስንተኛ ፡ የሚያነቃን ፡ ስንሰንፍ ፡ የሚያተጋን
ስንወድቅ ፡ የሚያነሳን ፡ ስንደክም ፡ የሚያበረታን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን (፪x)

ሙሴ ፡ ወይ ፡ ኢያሱ ፡ ኤልያስ ፡ ዼጥሮስ ፡ ቢሆን ፡ ዻውሎስ
ብቻ ፡ ጌታችን ፡ ሆይ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ አስነሳ ፡ በመንፈስ
አደባባይ ፡ ሞልቶ ፡ መፍሰሱ ፡ ምን ፡ አለው ፡ ቁም ፡ ነገር
አንተ ፡ የቀባኸው ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ይበቃል ፡ ለሀገር

አዝጌታ ፡ ሆይ (፪x) ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን
የእግዚአብሔር ፡ ቅባት ፡ ያለበት
ቢባርክ ፡ የሚደርስለት ፡ ቢረግምም ፡ የሚሆንለት
ጓዳችንን ፡ የምናሳየው ፡ ሚስጥራችንን ፡ የምናዋየው
በፍቅር ፡ የሚገስፀን ፡ በትዕግስት ፡ የሚሸከመን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን (፪x)