ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ (Keyesus Gar Nuro) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሕይወት ፡ እንደ ፡ ጥላ ፡ ሲያልፍ
ውበት ፡ እንደ ፡ ቅጠል ፡ ሲረግፍ
ያመኑበት ፡ ወዳጅ ፡ ሲከዳ
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሆኜ ፡ ልጐዳ

አዝ፡- ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል (፪x)
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል

አክሊል ፡ ከምደፋ ፡ በዓለም
የኢየሱስን ፡ መስቀል ፡ ልሸከም
ሰይጣን ፡ ከሚያቆላምጠኝ
ኢየሱሴ ፡ በእግሩ ፡ ይርገጠኝ

አዝ፡- ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል (፪x)
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል

ዙሪያዬን ፡ አጅቦኝ ፡ ወታደር
በቄሳር ፡ ሰገነት ፡ ከማደር
ደም ፡ እንባ ፡ እያፈሰስኩ ፡ ለጌታ
ይሻለኛል ፡ ለእኔስ ፡ ጐልጐታ

አዝ፡- ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል (፪x)
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል

በረደኝ ፡ አልልም ፡ ከንግዲህ
ራበኝ ፡ ጠማኝ ፡ አልል ፡ ከንግዲህ
አፌን ፡ በአፈር ፡ ውስጥ ፡ ቀብሬ
እኖራለሁ ፡ ቃሌን ፡ አክብሬ

አዝ፡- ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል (፪x)
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል


Navigation menu