Tamrat Haile/Egziabhier Terarayien Anagerew/Yajebe Sibeten

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


አዝ
አለኝ ወዳጅ የማይከዳ
ኑሮ ቢሆን ምድረ በዳ
የቀረበ ሲርቅ ያጀበ ሲበተን
ዞር ቀና ብዬ ሳይህ አላጣሁም አንተን

አብርሃም በእምነት ቢወጣ ከኡር
ተስፋው ቢረዝምበት ገባው ጥርጥር
የተረሳ ቢመስል ዘመኑም ያለፈ
ተስፋውን ፈጸምክለት ቃልህ መች ታጠፈ

አዝ
አለኝ ወዳጅ የማይከዳ
ኑሮ ቢሆን ምድረበዳ
የቀረበ ሲርቅ ያጀበ ሲበተን
ዞር ቀና ብዬ ሳይህ አላጣሁም አንተን

እንጀራ የበላ ፈውስ የተቀበለ
ፀሐይ ቆልቆል ሲል አንድ እንኳ የታለ (፪x)
የሰው አለኝታነት ዘለቄታ የለው
በሆሳእና ማግስት ስቀለው ስቀለው (፪x)

አዝ
አለኝ ወዳጅ የማይከዳ
ኑሮ ቢሆን ምድረ በዳ
የቀረበ ሲርቅ ያጀበ ሲበተን
ዞር ቀና ብዬ ሳይህ አላጣሁም አንተን

ኑሃሚን በሞአብ ህይወት ሲመራት
የልጇ ሚስት ኦርፋ ስማ ተለየቻት
ጊዜና ሁኔታ አላምር ሲላቸው
ስመው የሚለዩ ዛሬም ብዙ ናቸው (፪x)

አዝ
አለኝ ወዳጅ የማይከዳ
ኑሮ ቢሆን ምድረ በዳ
የቀረበ ሲርቅ ያጀበ ሲበተን
ዞር ቀና ብዬ ሳይህ አላጣሁም አንተን

ሳኦል ሰይፉን ሲስል በቤተ-መንግስቱ
ጋሻ ጃግሬዎቹም አብረው ሲዶልቱ (፪x)
ትልቁም ትንሹም ዳዊትን ሲያወግዝ
ማን ይሆን ዮናታን ምስኪኑን የሚያግዝ
ለምስኪኑ የሚያግዝ

አዝ
አለኝ ወዳጅ የማይከዳ
ኑሮ ቢሆን ምድረ በዳ
የቀረበ ሲርቅ ያጀበ ሲበተን
ዞር ቀና ብዬ ሳይህ አላጣሁም አንተን

ተስፋዬ ተሟጦ ቀን የጐደለ ዕለት
ባለዕዳ ሲመኘኝ ለዳግም ባርነት (፪x)
ሰማይም ነደደ ማድጋዬን ሞላው
እዳዬ ተከፍሎ ተረፈኝ የምበላው (፪x)

አዝ
አለኝ ወዳጅ የማይከዳ
ኑሮ ቢሆን ምድረ በዳ
የቀረበ ሲርቅ ያጀበ ሲበተን
ዞር ቀና ብዬ ሳይህ አላጣሁም አንተን