እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው (Egziabhier Terarayien Anagerew) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው
እንዲህ ፡ አለው (፫x)
"አንተ ፡ ተራራ ! ኧረ ፡ ለመሆኑ ፡ ምንድነህ?
በዘሩባቤል ፡ በልጄ ፡ ፊት ፡ ደልዳላ ፡ ሜዳ ፡ ትሆናለህ"
አለው (፫x) ፡ ናደው ፡ ደለደለው

ከእንግዲህስ ፡ ምን ፡ ሊበጀኝ ፡ እየየ ፡ ማለት ፡ ሰለቸኝ
አይደርሰኝም ፡ ወይ ፡ ወረፋ ፡ አይገድህም ፡ ወይ ፡ ስጠፋ
አምላካዊ ፡ መልስ ፡ ከሰማይ ፡ ዘሎ ፡ በኮረብታዎች ፡ ላይ
ዙሪያ ፡ ገባውን ፡ አበራው ፡ ተገፈተረ ፡ ተራራው

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው
እንዲህ ፡ አለው (፫x)
"አንተ ፡ ተራራ ! ኧረ ፡ ለመሆኑ ፡ ምንድነህ?
በዘሩባቤል ፡ በልጄ ፡ ፊት ፡ ደልዳላ ፡ ሜዳ ፡ ትሆናለህ"
አለው (፫x) ፡ ናደው ፡ ደለደለው

የኖራ ፡ ሜዳ ፡ ሃውልቱ ፡ ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ነዶ ፡ እሳቱ
ሊያጠፋኝ ፡ የተመኘው ፡ ጌታ ፡ በቁጣው ፡ ጐበኘው
ጠላት ፡ ለራሱ ፡ ቆፈረ ፡ ሊያስረኝ ፡ የወጣው ፡ ታሰረ
ሊበላኝ ፡ ያሻው ፡ ለራሱ ፡ ተበላ ፡ እኔ ፡ ግን ፡ አለሁ ፡ በተድላ

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው
እንዲህ ፡ አለው (፫x)
"አንተ ፡ ተራራ ! ኧረ ፡ ለመሆኑ ፡ ምንድነህ?
በዘሩባቤል ፡ በልጄ ፡ ፊት ፡ ደልዳላ ፡ ሜዳ ፡ ትሆናለህ"
አለው (፫x) ፡ ናደው ፡ ደለደለው

የብዙ ፡ ዘመን ፡ ጠላቴ ፡ ቆሞ ፡ የነበረው ፡ በፊቴ
ብርሃን ፡ እንዳላይ ፡ ከልሎ ፡ አየሁ ፡ በጌታዬ ፡ ተጥሎ
ጌታ ፡ በሰራው ፡ ከበረ ፡ መዝሙር ፡ በአፌ ፡ ጨመረ
ሰማይ ፡ ያጨብጭብ ፡ በደስታ ፡ ምድር ፡ ታክብረው ፡ በእልልታ

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው
እንዲህ ፡ አለው (፫x)
"አንተ ፡ ተራራ ! ኧረ ፡ ለመሆኑ ፡ ምንድነህ?
በዘሩባቤል ፡ በልጄ ፡ ፊት ፡ ደልዳላ ፡ ሜዳ ፡ ትሆናለህ"
አለው (፫x) ፡ ናደው ፡ ደለደለው


Navigation menu