Tamrat Haile/Egziabhier Awaqi New/Tamagn New Beqalu
ዘማሪ=ታምራት ፡ ሃይሌ ርዕስ=ታማኝ ነው በቃሉ
ወዳጄ አብርሃም ፊቴ ተመላለስ እኔን አይገደኝም ኪዳኔን ለማደስ እድሜህ ሮጦ ሮጦ ቢደርስልህ ከጫፍ ሰማይ ምድር ያልፋል የኔ ቃል አያልፍም አዝ ታማኝ (፫x) ታማኝ ነው እግዚአብሔር ፡ በቃሉ ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (፪x)
የማያልፍ ምን አለ እግዚአብሔር ከረዳ የእምነት ምንጭ ይሆናል ይሄ ምድረ በዳ ያለው ይሄድና ደግሞ ይመጣል ሌላ ግዙፉ ተራራ ይሆናል ደልዳላ አዝ
ታማኝ (፫x)
ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (፪x)
የመለኮት አዋጅ ከመጣ
ከሰማይ
ኢየሱስ ካዘዘ ይኬዳል ውኃ ላይ ሙታን ይነሳሉ እስራት ይፈታል ቁራሹ ተባርኮ ሺዎች ይበሉታል አዝ
ታማኝ (፫x)
ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (፪x)
ጌድዮንና ባርቅ ዮፍታሄና ሳምሶን ሳሙኤልና ዳዊት ጳውሎስና ጴጥሮስ የአንበሳን አፍ ዘጉ እሳት አልበላቸው ለታማኝነቱ ምስክሮች ናቸው አዝ ታማኝ (፫x) ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (፪x)
ምድያም በረሃ በፀሐይ ቃጠሎ በቁጥቋጦ እሳት ራዕይ አቀብሎ የፈርዖንን ክንድ በመቅሰፍት አድቅቆ አሻግሮ የለም ወይ ህዝቡን አስለቅቆ አዝ
ታማኝ (፫x)
ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (፪x)
ጉድጓዱን ቆፍረህ ውኃ ስታወጣ ዞርበል የኔ ነው ባይ ምቀኛ ቢመጣ እልፍ ብለህ ቆፍር ከሰው አትጣላ ርሆቦት ይሆናል የኋላ የኋላ አዝ
ታማኝ (፫x)
ታማኝ ነው እግዚአብሔር ፡ በቃሉ ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (፪x)