ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (Selam Eyesus New) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝሰላም (፫x) ፡ ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)

ደጁ ፡ ሳይከፈት ፡ ግድግዳው ፡ ሳይፈርስ
የሰላሙ ፡ ጌታ ፡ ገባ ፡ ኢየሱስ
ለተጨነቁቱ ፡ ግራ ፡ ለገባቸው
ሰላም ፡ ለእናንተ ፡ ይሁን ፡ ብሎ ፡ አሳረፋቸው

አዝሰላም (፫x) ፡ ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)

በጠመንጃ ፡ አፈ ፡ ሙዝ ፡ ወይ ፡ በእርቅ ፡ ድርድር
የተገኘ ፡ ሰላም ፡ አላየንም ፡ በምድር
ከዚህ ፡ የተቋጠረ ፡ ከዚያ ፡ ጋር ፡ ተፈታ
ስላልቀደመ ፡ ነው ፡ የሰላሙ ፡ ጌታ

አዝሰላም (፫x) ፡ ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)

የሃገር ፡ መሪዎች ፡ ክብር ፡ ሥልጣናቹህ
የውክልና ፡ ነው ፡ ወዶ ፡ የሰጣችሁ
ሞኝነት ፡ ቢመስልም ፡ ጌታን ፡ ተቀበሉ
ህዝቡን ፡ እንድመራ ፡ እኔን ፡ ምራ ፡ በሉ

አዝሰላም (፫x) ፡ ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)

አውራጃው ፡ ወረዳው ፡ ቀበሌም ፡ መንደሩ
ንግዱም ፡ ሃይማኖቱም ፡ እድር ፡ ማህበሩም
ምድር ፡ እንዲፈወስ ፡ አየር ፡ እንዲጠራ
ሁሉም ፡ እጁን ፡ ያንሳ ፡ ኢየሱስን ፡ ይጥራ

አዝሰላም (፫x) ፡ ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)

ምሁር ፡ ነህ ፡ ተማሪ ፡ ሃኪም ፡ ገበሬዉ
ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ጥሪው ፡ ላንተም ፡ ነው
የትዳርህ ፡ ኪዳን ፡ ጐጆህ ፡ አይፍረስ
የሰላሙ ፡ ሉዑል ፡ በቤትህ ፡ ይንገሥ

አዝሰላም (፫x) ፡ ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)

መጠጥና ፡ ዘፈን ፡ ጐበዝና ፡ ቆንጆው
አቃወሰህ ፡ ጤናህ ፡ አፈረሰ ፡ ጐጆው
ደግሞ ፡ የእሳት ፡ ፍርድ ፡ አለ ፡ ከዚህ ፡ የባሰዉ
የአምላክ ፡ ጥሪ ፡ ሰምቶ ፡ ላልተመለሰው

አዝሰላም (፫x) ፡ ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)


Navigation menu