ሌላ ፡ ነገር ፡ ይቅር (Liela Neger Yeqer) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሌላ ፡ ነገር ፡ ይቅር ፡ ይወራ ፡ ስለ ፡ እርሱ
በከበረው ፡ ደሙ ፡ ኃጢአት ፡ መደምሰሱ (፪x)
እንዳች ፡ ሳይባል ፡ ሁሉም ፡ ሰው ፡ ይመነው
ኢየሱስን ፡ ማጣት ፡ ሁሉንም ፡ ማጣት ፡ ነው (፪x)

የባህል ፡ እስርአት ፡ የኃጢአት ፡ ቁራኛ
እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ እያለን ፡ መዳኛ
ብርድና ፡ ኩነኔ ፡ ለከደነው ፡ ሁሉ
መቃብርን ፡ ከፋች ፡ ኢየሱስ ፡ አለ ፡ በሉ

አዝ፦ ትልቅ ፡ ስራ ፡ የተሰጠን ፡ ትልቅ ፡ ስራ
ስለኢየሱስ ፡ ሳንታክት ፡ ልናወራ
አንድ ፡ መንገድ ፡ አንድ ፡ እውነት ፡ አንድ ፡ ሕይወት
የተሰጠን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ከሠማያት

የእግዚአብሔርን ፡ ትዕዛዝ ፡ ቃሉን ፡ ስለናቅን
በአዳም ፡ መተላለፍ ፡ ሁሉም ፡ ሰው ፡ ወደቀ (፪x)
የዓለምን ፡ ኃጢአት ፡ በእንጨት ፡ ሊሸከም
ሥጋ ፡ ለብሶ ፡ መጣ ፡ ሁለተኛው ፡ አዳም (፪x)

ምርኮኛን ፡ የሚያስለቅቅ ፡ እስራት ፡ የሚያስፈታ
ምህረትን ፡ ይዞ ፡ የመጣውን ፡ ጌታ
አምኖ ፡ ይቀበለው ፡ የሰው ፡ ዘር ፡ በሙሉ
ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ የምስራች ፡ በሉ

አዝ፦ ትልቅ ፡ ስራ ፡ የተሰጠን ፡ ትልቅ ፡ ስራ
ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ሳንታክት ፡ ልናወራ
አንድ ፡ መንገድ ፡ አንድ ፡ እውነት ፡ አንድ ፡ ሕይወት
የተሰጠን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ከሠማያት

ሰይጣን ፡ የአገዛዝ ፡ ቀንበሩን ፡ ሲያከብድ
የዓለም ፡ እንቆቅልሽ ፡ እየበዛ ፡ ሲሄድ (፪x)
ኃያላን ፡ ነገሥታት ፡ ፈላስፎች ፡ ቢሆኑ
ሊያድን ፡ የተቻለው ፡ ማነው ፡ ለመሆኑ (፪x)

የመዳንን ፡ እራስ ፡ በመስቀል ፡ ፈጽሞ
ቤት ፡ ሊያዘጋጅልን ፡ የሄደልን ፡ ቀድሞ
በሕያዋን ፡ በሙታን ፡ ሊፈርድ ፡ የሚመጣው
የጽዮን ፡ ሙሽራ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

አዝ፦ ትልቅ ፡ ስራ ፡ የተሰጠን ፡ ትልቅ ፡ ስራ
ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ሳንታክት ፡ ልናወራ
አንድ ፡ መንገድ ፡ አንድ ፡ እውነት ፡ አንድ ፡ ሕይወት
የተሰጠን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ከሠማያት


Navigation menu