እስከ ፡ ዛሬ ፡ የጠበቀኝ (Eske Zarie Yetebeqegn) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

እስከዛሬ ፡ የጠበቀኝ ፡ በእጁ ፡ ይዞ ፡ ያለቀቀኝ
የክርስትናን ፡ ቀጭን ፡ መንገድ ፡ የሕይወትን ፡ ውጣ ፡ ውረድ
ባይበዛልኝ ፡ የእርሱ ፡ ፀጋ ፡ አንዷም ፡ ሌሊት ፡ አትነጋ
ዛሬም ፡ ቆምኩኝ ፡ በዚህ ፡ ቦታ ፡ ስሙ ፡ ይክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x)

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ አላለቀምና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ከቶ ፡ አያልቅምና

እንደጠላት ፡ አሳብ ፡ ቢሆን ፡ ከሆነልኝ ፡ አንዱም ፡ አይሆን
ታሪክ ፡ ቢያብብ ፡ ሕይወት ፡ ቢያምር ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ በእርሱ ፡ ተዐምር
ከእያንዳንዷ ፡ እስትንፋስ ፡ ስጦታ ፡ ናት ፡ የኢየሱስ
ከፈቀደ ፡ ይሁን ፡ ካለ ፡ አይሆንም ፡ የሚል ፡ ማን ፡ አለ (፪x)

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ አላለቀምና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ከቶ ፡ አያልቅምና

አንተ ፡ . (1) . ፡ ቀናተኛ ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ አትተኛ
እንደተራበ ፡ አንበሳ ፡ ዙሪያዬን ፡ ብትዞር ፡ እያገሳህ
ልትውጠኝ ፡ ብትመኘኝ ፡ ሲያምርህ ፡ ይቅር ፡ አታገኘኝ
በስሙ ፡ አጥር ፡ በደሙ ፡ እሳት ፡ ከልሎኛል ፡ የእኔ ፡ አባት (፪x)

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ አላለቀምና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ከቶ ፡ አያልቅምና

ያንን ፡ ዘንዶ ፡ እባቡን ፡ የወጋኸው ፡ ወገቡን
ራስ ፡ እራሱን ፡ ያስረገጥከኝ ፡ ስንቱን ፡ ነገር ፡ ያስመለጥከኝ
ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ጋሻዬ ፡ በክፉ ፡ ቀን ፡ መሸሺያዬ
መቆሚያዬ ፡ ነህ ፡ አለቴ ፡ ላመስግንህ ፡ በአንደበቴ (፪x)

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ አላለቀምና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ከቶ ፡ አያልቅምና


Navigation menu