በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ (Bemesgana Hulu Lay) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ስምህ
ይባረክ ፡ ይባረክ ፤ ይባረክ ፡ ይባረክ (፪x)

ቅዱሳን ፡ መላዕክት ፡ ሱራፌል ፡ በሠማይ ፡ ያሉ
ሳያቋርጡ ፡ ዘወትር ፡ ለአንተ ፡ ይሰግዳሉ
ፀሐይ ፡ ጨረቃ ፡ ከዋክብት ፡ ቁጥር ፡ የሌላቸው
በቀን ፡ በማታ ፡ እንዲያበሩ ፡ የፈጠርካቸው
የጥበብህ ፡ ስራ ፡ ምሳሌ ፡ ናቸው

አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ስምህ
ይባረክ ፡ ይባረክ ፤ ይባረክ ፡ ይባረክ (፪x)

ደማናዎችህ ፡ እንደጥጥ ፡ የተባዘቱ
ማሰሮው ፡ ሲያዘነብል ፡ በልጉ ፡ ክረምቱ
የሠማይ ፡ አዕዋፍ ፡ በየዘር ፡ በየወገኑ
ማን ፡ ይናገራል ፡ የዕውቀትህ ፡ ልኩ ፡ መጠኑ
በየቋንቋቸው ፡ ሲያመሰግኑህ

አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ስምህ
ይባረክ ፡ ይባረክ ፤ ይባረክ ፡ ይባረክ (፪x)

የምድር ፡ ፍጥረታት ፡ ሕያዋን ፡ ተንቀሳቃሾች
ሰዎች ፡ እንስሳት ፡ አራዊት ፡ የባሕር ፡ አሶች
ውቅያኖስ ፡ ወንዙ ፡ ሸለቆው ፡ ደኑ ፡ ተራራ
አቤት ፡ ሲያስደንቅ ፡ የቃልህ ፡ የእጅህ ፡ ስራ
ሁሉም ፡ በቋንቋው ፡ ክብርህን ፡ ያውራ

አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ስምህ
ይባረክ ፡ ይባረክ ፤ ይባረክ ፡ ይባረክ (፪x)

በዓለም ፡ ታሪክ ፡ በዘመን ፡ በአመታት ፡ መሃል
የሌለህበት ፡ ያለአንተስ ፡ የሆነ ፡ የታል
ነገሥታት ፡ ሲያልፉ ፡ ኃያላን ፡ ወድቀው ፡ ሲቀሩ
ድንቅ ፡ የተባሉ ፡ ግኝቶች ፡ ሲያልፉ ፡ ሲሻሩ
የእኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በክብሩ

አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ስምህ
ይባረክ ፡ ይባረክ ፤ ይባረክ ፡ ይባረክ (፪x)

አቤቱ ፡ ስራህ ፡ አሳብህ ፡ ሁሉም ፡ ድንቅ ፡ ነው
ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ሚይስደንቅ ፡ መዳናችን ፡ ነው
በመጀመሪያ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ የነበረው ፡ ቃል
በድንግል ፡ ማህጸን ፡ ሰው ፡ ሆኖ ፡ መድን ፡ ተወልዷል
ጨካኙን ፡ ዘንዱ ፡ በመስቀል ፡ ራሱን ፡ ቀጥቅጦ
አመተ ፡ ፍዳን ፡ በአመተ ፡ ምህረት ፡ ለውጦ
ሁሉን ፡ ድል ፡ አድርጐ ፡ በቀኝህ ፡ ለተቀመጠው
በክብር ፡ በሥልጣን ፡ ዳግመኛ ፡ ለሚገለጠው
ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ውዳሴ ፡ ይኸው

አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ስምህ
ይባረክ ፡ ይባረክ ፤ ይባረክ ፡ ይባረክ (፫x)
ይባረክ ፡ ይባረክ ፤ ይባረክ ፡ ይባረክ


Navigation menu