በድብብቆሽ ፡ ቀኑ ፡ እንዳያልፍ (Bedebebeqosh Qenu Endayalf) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሰርግና ፡ ምላሹ ፡ ድግሱ ፡ ቀለጠ
ከትላንቱ ፡ አጀብ ፡ የዛሬው ፡ በለጠ
የፍቅር ፡ ጨዋታው ፡ ከመቼው ፡ አለቀ
የፍቺ ፡ ጥያቄ ፡ ፍርድ ፡ ቤት ፡ ዘለቀ
ጭብጨባው ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ዕልልታም ፡ ባልከፋ
አስቸገረን ፡ እንጂ ፡ አንገት ፡ እያስደፋ (፪x)

ትዳር ፡ ይከበር ፡ ቃልኪዳን ፡ ይጽና
በመካከሉ ፡ አምላክ ፡ አለና
መፋታትን ፡ እጠላለሁ ፡ ብሏልና

ስብከት ፡ ሙያ ፡ ሆኖ ፡ ወንጌልም ፡ ለእንጀራ
መዝሙሯ ፡ ጸሎቷም ፡ . (1) . ፡ ተቸርችራ
ገበያው ፡ ቀለጠ ፡ ቤተመቅደስ ፡ ደጃፍ
ጌታ ፡ ተመልሶ ፡ እስኪያነሳ ፡ ጅራፍ
ምን ፡ ትጠብቃለህ ፡ ሰብስብ ፡ ኮተትህን
ያሸጥሃል ፡ ኋላ ፡ በኩርነትህን (፪x)

ወንጌል ፡ ይሰበክ ፡ በእውነት ፡ በጽድቅ
በድብብቆሽ ፡ ቀኑ ፡ እንዳያልቅ
መክሊት ፡ ሰጪ ፡ አለ ፡ ጌታ ፡ ሚጠይቅ

ወንድሞች ፡ ተጣሉ ፡ በመሪነት ፡ ሰበብ
ያውም ፡ በመድረኩ ፡ ጉድ ፡ እን
ሽማግሌም ፡ ልግዛ ፡ መጋቢው ፡ ልንገሥ
በኧረኞች ፡ ትግል ፡ መንጋ ፡ ሲታመስ
በብዕር ፡ በቃላት ፡ ጦፈ ፡ ክርክሩ
እስቲ ፡ መልሱልኝ ፡ የማነው ፡ ወንበሩ (፪x)

መንጋው ፡ የኢየሱስ ፡ የሞተለት
የበረቱን ፡ ቁልፍ ፡ አስረክቡት
የእኛ ፡ ጥሪ ፡ ዝቅታ ፡ ነው ፡ ሎሌነት

ነጭ ፡ ጥቁር ፡ ቀለም ፡ መለየት ፡ አቅቶት
ድንበር ፡ የጣሰ ፡ ይላል ፡ ምናለበት
ጽድቅ ፡ ከአመጽ ፡ ጋር ፡ ብርሃን ፡ ከጨለማ
አምላክ ፡ ያጣላውን ፡ ማን ፡ አለህ ፡ አስማማ
ይልቅ ፡ ከዓለም ፡ ተለይ ፡ ውጣ ፡ ተቀደስ
የትም ፡ እየረገጥክ ፡ ቤቱን ፡ አታርክስ (፪x)

እልፍ ፡ በል ፡ ውጣ ፡ ተለይ
ስሙ ፡ ተጠርቷል ፡ በአንተ ፡ ላይ
የሚመጣ ፡ ሙሽራ ፡ አለህ ፡ ከሠማይ

ሆድም ፡ ለመብል ፡ ነው ፡ መብልም ፡ ለሆድ
ሁሉም ፡ ይጠፋሉ ፡ ብንወድም ፡ ባንወድ
አንዳንዴም ፡ በመጾም ፡ ጐሽም ፡ ሥጋህን
አብልቶ ፡ ከሚዘርፍ ፡ አስጥል ፡ ፀጋህን
እንቅልፍም ፡ አይብዛ ፡ አርግለት ፡ ገደብ
ጸሎት ፡ አይረሳ ፡ ቃሉም ፡ ይነበብ (፪x)

ተነስ ፡ ተጋደል ፡ ጸንተህ ፡ ተዋጋ
ያበረታሃል ፡ የአምላክህ ፡ ፀጋ
የትም ፡ መቼም ፡ ጌታ ፡ እንዳለ ፡ አትዘንጋ


Navigation menu