Tamrat Haile/Ahunem Alehu Bemerkebu/Ahunem Alehu Bemerkebu

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ታምራት ሃይሌ ርዕስ አሁንም አለሁ በመርከቡ አልበም አሁንም አለሁ በመርከቡ

አዝ አሁንም አለሁ በመርከቡ ገና አልደረሰም ከወደቡ መውረድ አልሻም እጓዛለሁ ውኋ እንዳይበላኝ እፈራለሁ

ተሳፍሬአለሁ በባቡሩ ገና አልደረሰም ከሰፈሩ መቆም አልሻም በመንገዱ ይቆራርጣል ሐዲዱ

አዝ አሁንም አለሁ በመርከቡ ገና አልደረሰም ከወደቡ መውረድ አልሻም እጓዛለሁ ውኋ እንዳይበላኝ እፈራለሁ

ስንቶች ተጓዙ ከእኔ ጋራ ሸለቆ ወርደው ወጡ ተራራ እየመሰለኝ ከጐኔ እያሉ እኔ መች አወቅሁ እንደተበሉ

አዝ አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ ገና አልደረሰም ከወደቡ መውረድ አልሻም እጓዛለሁ ውኋ እንዳይበላኝ እፈራለሁ

ሳይመርምሩ ጊዜ ዘመኑን ሳያውቁት ውኋው ጥልቅ መሆኑን መንሸራሸር እያማራቸው ሳያውቁት ድንገት ውጦ አስቀራቸው

አዝ አሁንም አለሁ በመርከቡ ገና አልደረሰም ከወደቡ መውረድ አልሻም እጓዛለሁ ውኋ እንዳይበላኝ እፈራለሁ

ስንቱን አልፌ እዚህ መድረሴ በፀጋው እንጂ መቼ በራሴ ጌታ ሰጥቶኛል አቅሜን መለኪያ ከፀጋው በቀር ያለኝ መመኪያ

አዝ አሁንም አለሁ በመርከቡ ገና አልደረሰም ከወደቡ መውረድ አልሻም እጓዛለሁ ውኋ እንዳይበላኝ እፈራለሁ

መርከቡ ሲቆም በየወደቡ ወራጁን ሲያወርድ ሌሎች ሲገቡ በየከተማው ባቡሩም ሲያልፍ እንዱን ሲያሳፍር ሌላውን ሲያራግፍ ከጫፍ የሚደርስ ማን ይሆን እንጃ አጽናኝ እያልኩኝ ይዣለሁ ምልጃ

አዝ አሁንም አለሁ በመርከቡ ገና አልደረሰም ከወደቡ መውረድ አልሻም እጓዛለሁ ውኋ እንዳይበላኝ እፈራለሁ