ይገርማል (Yegermal) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 1.png


(1)

ይገርማል
(Yegermal)

ዓ.ም. (Year): 2005
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
ምንም ፡ ክፍያ ፡ አልከፈልኩም
ከላይ ፡ ወደታችም ፡ አላልኩም
በጓደኛም ፡ ዘመድ ፡ አልመጣሁም
ጌታን ፡ ለማግኘት ፡ አልደከምኩም

በፍቅር ፡ ቃሉ ፡ ሲናገረኝ
እወድሃልሁ ፡ ብሎ ፡ ሲለኝ
እጅግ ፡ ተገረምኩ ፡ ተደነቅኩ
እንዲህ ፡ ያለ ፡ ሰው ፡ ማነው ፡ አልኩ

ያለ ፡ የነበረ ፡ የሚኖረው
ኤልሻዳዩ ፡ ጌታ ፡ ለካስ (፫x) ፡ ለካስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ጌታ ፡ ለካስ ፡ ለካስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

ይገርማል ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ይገርማል
ይደንቃል ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ይደንቃል
ሳልመርጠው ፡ ኢየሱስ ፡ መርጦኛል
ሳልወደው ፡ እንዲህ ፡ ወዶኛል
ከሞት ፡ መካከል ፡ ነጥቆ ፡ አውጥቶኛል

አዝ:- ሳመሰግነው ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ
ስዘምርለት ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ
እልል ፡ ስልለት ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ
ያደረገልኝን ፡ እያየሁ

አምኜ ፡ በድንገት ፡ ያገኘሁት
ሕይወቴን ፡ ሁሉ ፡ የሰጠሁት
ይኸው ፡ እስካሁን ፡ ይመራኛል
ደግሞም ፡ ዘላለም ፡ ያኖረኛል
ከእጆቹ ፡ መሃል ፡ ማን ፡ ያወጣኛል
ከእጁ ፡ ፈልቅቆ ፡ ማን ፡ ይወደኛል

ይበልጣል ፡ ከሁሉም ፡ ይበልጣል
ይመረጣል ፡ ኢየሱሴ ፡ ይመረጣል
መች ፡ አሳልፎ ፡ ይሰጣል ፡ ስሙ ፡ ከስሞች ፡ ይበልጣል
ኢየሱን ፡ ጠርቶ ፡ ማን ፡ አፍሮ ፡ ያውቃል

አዝ:- ሳመሰግነው ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ
ስዘምርለት ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ
እልል ፡ ስልለት ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ
ያደረገልኝን ፡ እያየሁ (፪x)

የክብር ፡ ጌታ ፡ ድንቅ ፡ አረገ ፣ አቤት ፡ ዲያቢሎስ ፡ ተናደደ
ውስጠ ፡ ሚስጥሩም ፡ ተገለጠ ፣ የጋረደውም ፡ ተቀደደ
አሁን ፡ ምን ፡ ይበል ፡ ምን ፡ ይዋጠው
ኢየሱስ ፡ ማንነቱን ፡ ሲገልጠው
(፪x)

ይነድዳል ፡ እሳቱ ፡ ይነድዳል ፣ ይዋረዳል ፡ ዲያቢሎስ ፡ ይዋረዳል
መች ፡ በዚህ ፡ ብቻ ፡ ያበቃል ፣ የያዘውን ፡ ሁሉ ፡ ይለቃል
ማሳወር ፡ እንጂ ፡ እሱ ፡ ማብራት ፡ የት ፡ ያውቃል
ማዋረድ ፡ እንጂ ፡ እሱ ፡ ማክበር ፡ የት ፡ ይውቃል

አዝ:- ሳመሰግነው ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ
ስዘምርለት ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ
እልል ፡ ስልለት ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ
ያደረገልኝን ፡ እያየሁ (፪x)

እስኪ ፡ እንደኔ ፡ ጌታ ፡ የሰራላችሁ
በምድረ ፡ በዳ ፡ ውሃ ፡ የሰጣችሁ
ይሰማ ፡ ዛሬ ፡ እልልታችሁ
ፈጽሞ ፡ አይቆጠብ ፡ ድምጻችሁ (ፈጽሞ ፡ አይቆጠብ ፡ ድምጻችሁ)

እስኪ ፡ እንደኔ ፡ ጌታ ፡ የሰራላችሁ
በጨለማ ፡ ውስጥ ፡ ብርሃን ፡ የሆናችሁ
ይሰማ ፡ ዛሬ ፡ እልልታችሁ
ፈጽሞ ፡ አይቆጠብ ፡ ድምጻችሁ (ፈጽሞ ፡ አይቆጠብ ፡ ድምጻችሁ)


Navigation menu