ቅዱስ ፡ ቅዱስ (Qedus Qedus) - ሶፍያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሶፍያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 3.jpg


(3)

ፍጠንልኝ
(Fetenelegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 7:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፍያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

አቤቱ ፡ እንዴት ፡ ቅዱስ ፡ ነህ (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እንዴት ፡ ቅዱስ ፡ ነህ
አቤቱ ፡ እንዴት ፡ ቅዱስ ፡ ነህ (፫x)
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ እንዴት ፡ ቅዱስ ፡ ነህ
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እንዴት ፡ ቅዱስ ፡ ነህ

ሰው ፡ ሁሉ ፡ በድሏል ፡ ሃጥያትንም ፡ ሰርቷል
ጻድቅ ፡ የለም ፡ ማንም ፡ ክብርህ ፡ ጎሎበታል
አንተ ፡ ራስህ ፡ ፈቅደህ ፡ ባትቀድሰው ፡ ኖሮ
ማን ፡ ይጠጋ ፡ ነበር ፡ ወደ ፡ ፊትህ ፡ ደፍሮ

ነቀፋ ፡ የሌለብህ ፡ ቅዱስ
ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቅዱስ
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ ቅዱስ
ነገም ፡ ለዘላለም ፡ ቅዱስ

ነውር ፡ የሌለብህ ፡ ቅዱስ
ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቅዱስ
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ ቅዱስ
ነገም ፡ ለዘላለም ፡ ቅዱስ

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
ቅዱስ ፡ ቅዱስ
ቅዱስ ፡ ቅዱስ

አቤቱ ፡ እንዴት ፡ ቅዱስ ፡ ነህ (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እንዴት ፡ ቅዱስ ፡ ነህ
አቤቱ ፡ እንዴት ፡ ቅዱስ ፡ ነህ (፫x)
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ እንዴት ፡ ቅዱስ ፡ ነህ
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እንዴት ፡ ቅዱስ ፡ ነህ

መላዕክትህ ፡ እጅግ ፡ ቅዱሳን ፡ ሲሆኑ
አቅም:ከሰሳቸው:አንተ ፡ ፊት ፡ ሲቆሙ
እንደሰማይ ፡ ጥራት ፡ ቅዱስ ፡ ነን ፡ ብልህ
ሰማያት ፡ ከፊትህ ፡ ብጹሃን ፡ አይደሉም

በምን ፡ ይመሰላል ፡ ቅድስናህ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ አልተገኘምና

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
ቅዱስ ፡ ቅዱስ
ቅዱስ ፡ ቅዱስ

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
ቅዱስ ፡ ቅዱስ
ቅዱስ ፡ ቅዱስ

(ቅዱስ (፬x) ፡ ቅዱስ (፫x))