Shewaye Damte

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ልባችንን የመንፈስህ ማደረያ ሀጢያት አሻገተው መቅደስህን ተነስ ጌታ ሆይ አፅዳው ስጋችንን ግታው እንደ ሎጥ እንደ ኖህ ዘመን ሀጢይትን እጅግ አበዛን ጌታ ሆይ እባክህ ገስፀን አባት ነህን ቆንጥጠን ስንጠፋ ዝም አትበለን*2

ደግመህ ደግመህ ስቀለው ስጋችንን እንምሰልህ አንተን በመንፈስህ የጀመርነው ጉዟችን ለሂወት ይሁንልን እንደ ሎጥ እንደ ኖህ ዘመን ሀጢይትን እጅግ አበዛን ጌታ ሆይ እባክህ ገስፀን አባት ነህን ቆንጥጠን ስንጠፋ ዝም አትበለን*2

ቅዱስ ስምህን አረግነው መነገጃ ብር ወርቅን ማረፊያ መኖራችን ነበረ ለአለም ብርሀን ጨለማ ሆነናል እንደ ሎጥ እንደ ኖህ ዘመን ሀጢያትን እጅግ አበዛን ጌታ ሆይ እባክህ ገስፀን አባት ነህን ቆንጥጠን ስንጠፋ ዝም አትበለን*2

በሰናኦር ግንባችንን ሰርተናል እጅግ ተኩራርተናል ሀጢያት ለብሰን አመፃን ደርበናል ፈውስ ይስፈልገናል እንደ ሎጥ እንደ ኖህ ዘመን ሀጢይትን እጅግ አበዛን ጌታ ሆይ እባክህ ገስፀን አባት ነህን ቆንጥጠን ስንጠፋ ዝም አትበለን*2

|ዘማሪ=ሸዋዬ፡ዳምጤ |Artist=Shewaye Damte }}