ልበል ፡ እንደ ፡ ማሪያም (Lebel Ende Mariyam) - ሰናይት ፡ እንግዳ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሰናይት ፡ እንግዳ
(Senait Engeda)

Lyrics.jpg


(3)

ኢየሱስ ፡ ትክክል
(Eyesus Tekekel)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 7:18
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰናይት ፡ እንግዳ ፡ አልበሞች
(Albums by Senait Engeda)

አዝ፦ ልበል ፡ እንደ ፡ ማርያም ፡ ሚላችሁን ፡ አርጉ
እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ አንዳች ፡ እንዳትሰጉ
አንድ ፡ ነገር ፡ ብቻ ፡ አሃሃ ፡ አውቃለሁ ፡ ገብቶኛል
ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ካለ ፡ እሰይ ፡ ይበቃኛል (፪x)

ሰዎች ፡ ሰርግ ፡ ደግሰው ፡ እጅግ ፡ በሰፊው
የወይን ፡ ጠጁ ፡ አልቆ ፡ ጉድ ፡ አረጋቸው
ሲወጡ ፡ ሲገቡ ፡ ተጨንቀው ፡ እያለ
የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ አሃሃ ፡ ለካስ ፡ እዚያ ፡ ቤት ፡ አለ
ኢየሱስ ፡ ጣልቃ ፡ ገባ ፡ ዲያብሎስ ፡ ከሰረ
ውሃው ፡ ግሩም ፡ ጣዕም ፡ ያለው ፡ ወይን ፡ ጠጅ ፡ ሆነ

አዝ፦ ልበል ፡ እንደ ፡ ማርያም ፡ ሚላችሁን ፡ አርጉ
እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ አሜን ፡ አንዳች ፡ እንዳትሰጉ
አንድ ፡ ነገር ፡ ብቻ ፡ አሃሃ ፡ አውቃለሁ ፡ ገብቶኛል
ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ካለ ፡ አሜን ፡ ይበቃኛል

ወገኖች ፡ እኛንም ፡ ችግር ፡ ሲገጥመን
እንበለው ፡ እንደዚህ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስን
ኢየሱሴ ፡ ግባ ፡ በቤቴ ፡ ታደም
ኑሮዬ ፡ ያለአንተ ፡ አሃሃ ፡ ትርጉም ፡ የለውም
ብቻ ፡ ይሁን ፡ እንጂ ፡ እርሱ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
ደልዳላ ፡ ይሆናል ፡ ትልቁ ፡ ተራራ

አዝ፦ ልበል ፡ እንደ ፡ ማርያም ፡ ሚላችሁን ፡ አርጉ
እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ አሜን ፡ አንዳች ፡ እንዳትሰጉ
አንድ ፡ ነገር ፡ ብቻ ፡ አሃሃ ፡ አውቃለሁ ፡ ገብቶኛል
ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ካለ ፡ አሜን ፡ ይበቃኛል

የኢየሱስ ፡ ወዳጅ ፡ ድንገት ፡ ታመመና
ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ ላኩ ፡ ብለው ፡ በቶሎ ፡ ና
ጌታም ፡ አልፈጠነ ፡ አሃሃ ፡ አለአዛርም ፡ ሞተ
አራት ፡ ቀን ፡ ሆነው ፡ ተቀብሮ ፡ ሸተተ
ቢዘገይም ፡ እንኳን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መጣ
የሞተው ፡ ከቀብሩ ፡ ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ወጣ

አዝ፦ ልበል ፡ እንደ ፡ ማርያም ፡ ሚላችሁን ፡ አርጉ
እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ አሜን ፡ አንዳች ፡ እንዳትሰጉ
አንድ ፡ ነገር ፡ ብቻ ፡ አሃሃ ፡ አውቃለሁ ፡ ገብቶኛል
ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ካለ ፡ ይሁን ፡ ይበቃኛል

ዝናቡ ፡ ፀሃዯ ፡ ነፋሱ ፡ አየሩ
እንዳስፈለጋችሁ ፡ ብትቀያየሩ
ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው ፡ ምንድን ፡ ያስፈራኛል
ቁራን ፡ እየላከ ፡ ቢያስፈልግ ፡ ጮማን ፡ ያበላኛል
ስደክም ፡ ኃይል ፡ ሰጥቶ ፡ ስወደቅ ፡ አንስቶ
ቤቱ ፡ ያደርሰኛል ፡ ሃያል ፡ ክንዱ ፡ መርቶ

አዝ፦ ልበል ፡ እንደ ፡ ማርያም ፡ ሚላችሁን ፡ አርጉ
እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ አሜን ፡ አንዳች ፡ እንዳትሰጉ
አንድ ፡ ነገር ፡ ብቻ ፡ አሃሃ ፡ አውቃለሁ ፡ ገብቶኛል
ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ካለ ፡ እሰይ ፡ ይበቃኛል (፫x)