የከበረ (Yekebere) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)


(3)

ምሳሌ ፡ የሌለህ
(Misale Yeleleh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:57
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

የከበረ ፡ ከሁሉ ፡ የተሻለ
የከበረ ፡ ከሁሉ ፡ የተሻለ
ሰውነቴ ፡ ለአንተ ፡ አቀርባለሁ (፪x)
እኔነቴን ፡ ለአንተ ፡ አቀርባለሁ (፪x)

መሰዊያን ፡ ሰራሁ ፡ ልሰዋልህ ፡ በፊትህ ፡ ላቀርበው
ያለኝን ፡ በሙሉ ፡ ታውቀዋለህ ፡ የቱን ፡ ነው ፡ ምትሻው
እያልኩኝ ፡ ስደረድር ፡ ምድርና ፡ ሞላዋ ፡ ለካስ ፡ የአንተ ፡ ነው
የሚቃጠል ፡ መስዋዕት ፡ ደስ ፡ እንዳያሰኝህ ፡ ይህንን ፡ ተረዳሁ

ታዲያ ፡ እኔም ፡ ምኔን ፡ ልስጥህ
ምን ፡ ሰጥቼ/ሰውቼ ፡ ደስ ፡ ላሰኝህ
እያልኩኝ ፡ ስጠይቅ ፡ ቃልህን
ስጠው/ሰዋው ፡ አለኝ ፡ እራስህን (፪x)

ስለዚህ ፡ እራሴን ፡ ሕያውና ፡ ቅዱስ ፡ አድርጌ
ፊትህን ፡ ደስ ፡ እንዳሰኘሁ ፡ ፈቀድኩኝ ፡ ልሰዋ ፡ ይኸው
ልዩ ፡ ጣዕም ፡ የመዓዛ ፡ ሽታ
ሆኜ ፡ ልቅረብ ፡ በፊትህ ፡ ጎይታ

ከሚቃጠል ፡ መስዋዕት ፡ ጋራ ፡ ወደፊትህ ፡ እመጣለሁ
የአምልኮዬ ፡ መዓዛ ፡ ሽታ ፡ ዙፋንህን ፡ ይክበበው
በምህረት ፡ የተሞላህ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ ነህና
አሁንም ፡ አበዛለሁ ፡ ከነፍሴ ፡ ምሥጋና

ኦ ፡ በምሥጋና ፡ በዝማሬ ፡ እመጣለሁ
ኦሆሆ ፡ ወደ ፡ ማደሪያህ ፡ እገባለሁ (፮x)