ምሥጋና. (Mesgana.) - ሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ
(Samuel Borsamo)

Lyrics.jpg


(2)

በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
(Begieta Hulu Yechalal)

ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Borsamo)

 
በመገረፉ ፡ ቁስል ፡ ቁስሎቼን ፡ ፈውሶ
በፍቅር ፡ እጆቹ ፡ እምባዬን ፡ አብሶ
ይህን ፡ ከዚህ ፡ ዘመን ፡ በሰላም ፡ እዘረጋለሁ???
ለመረጠኝ ፡ አምላክ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ

አዝ፦ ምሥጋና (፫x) ፡ የጌታዬን ፡ ማዳን ፡ አይቻለሁና
ምሥጋና (፫x) ፡ የአምላኬን ፡ ማዳን ፡ አይቻለሁና

የገማ ፡ ቢኖርም ፡ አራት ፡ ቀን ፡ ያለፈው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ የትንሳኤ ፡ አምላክ ፡ ነው
ለእኔ ፡ ሲከብድብኝ ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ እሮጣለሁ
መቅረዙ ፡ ተፈቶ ፡ ሕያው ፡ ሆኖ ፡ አያለሁ

አዝ፦ ምሥጋና (፫x) ፡ የጌታዬን ፡ ማዳን ፡ አይቻለሁና
ምሥጋና (፫x) ፡ የአምላኬን ፡ ማዳን ፡ አይቻለሁና

የቁጣ ፡ ግልምጫ ፡ የክፋት ፡ እርግጫ
ቢፈራረቅ ፡ እንኳን ፡ የግፈኞች ፡ ቁጫ???
ከላይ ፡ የሚያይ ፡ ጌታ ፡ በጥማት ፡ ስንጫጫ
የማዕዘኑ ፡ አለት ፡ ሆኖኛል ፡ ማምለጫ

አዝ፦ ምሥጋና (፫x) ፡ የጌታዬን ፡ ማዳን ፡ አይቻለሁና
ምሥጋና (፫x) ፡ የአምላኬን ፡ ማዳን ፡ አይቻለሁና

ቀኖች ፡ ክፋታቸው ፡ እጥፍ ፡ ቢጨምሩ
የማመልከው ፡ አምላክ ፡ ይበልጣል ፡ ከሁሉ
ይሄ ፡ ብልጭልጩ ፡ ሁሉ ፡ ነገር ፡ ሲያልቅ
ውዴ ፡ ከተፍ ፡ ይላል ፡ ልጆቹን ፡ ሊያሳርፍ

አዝ፦ ምሥጋና (፫x) ፡ የጌታዬን ፡ ማዳን ፡ አይቻለሁና
ምሥጋና (፫x) ፡ የጌታዬን ፡ ማዳን ፡ አይቻለሁና


Navigation menu