ለብቻዬ (Lebechayie) - ናትናኤል ፡ ዓለሙ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ናትናኤል ፡ ዓለሙ
(Natnael Alemu)
ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2015)
ርዝመት (Len.): 6:37
ሌሎች ፡ ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(Other Singles)
ሌሎች ፡ የናትናኤል ፡ ዓለሙ ፡ አልበሞች
(Other Albums ፡ by Natnael Alemu)

አዝ፦ ባለህ ፡ ያልኩት ፡ ለታ ፡ መች ፡ ከጐኔ ፡ ሆኗል
የቅርቤ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ያልኩት ፡ እንዳላየኝ ፡ አልፏል
ግን ፡ አንድ ፡ አለ ፡ ወዳጅ ፡ ሁሉም ፡ ሲሄድ ፡ ከእኔ
ያኔ ፡ ለብቻዬ ፡ ሆነልኝ ፡ ከጐኔ

ለብቻዬ (፪x)
አልተውከኝም ፡ እኔን ፡ ለብቻዬ
ለብቻዬ (፪x)
መች ፡ ተውከኝ ፡ እኔን ፡ ለብቻዬ

ፍቅሩ ፡ ጤዛ ፡ አይደለም ፡ የማለዳ ፡ ብቻ
አይገኝለትም ፡ መውደዱ ፡ ዳርቻ
ፀሐይ ፡ አዘቅዝቃ ፡ ዋ ፡ እኔ ፡ ዋ ፡ እኔ ፡ እያልኩኝ
ያኔ ፡ በዚያን ፡ ጊዜ ፡ ኢየሱስ ፡ አልራቀኝ

ወዳጅ ፡ ለእኔስ ፡ ወዳጅ
ወዳጅ ፡ ሆነህልኛል
ልቤን ፡ ሀዘን ፡ ጐድቶት
ደርሰህ ፡ አጽናንተኸኛል (፪x)

አዝ፦ ባለህ ፡ ያልኩት ፡ ለታ ፡ መች ፡ ከጐኔ ፡ ሆኗል
የቅርቤ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ያልኩት ፡ እንዳላየኝ ፡ አልፏል
ግን ፡ አንድ ፡ አለ ፡ ወዳጅ ፡ ሁሉም ፡ ሲሄድ ፡ ከእኔ
ያኔ ፡ ለብቻዬ ፡ ሆነልኝ ፡ ከጐኔ

ለብቻዬ (፪x)
አልተውከኝም ፡ እኔን ፡ ለብቻዬ
ለብቻዬ (፪x)
መች ፡ ተውከኝ ፡ እኔን ፡ ለብቻዬ

የወጠኑት ፡ ሳይሆን ፡ የያዙት ፡ ሲጠፋ
ልብን ፡ ያሳዝናል ፡ ያስቆርጣል ፡ ተስፋ
ግን ፡ ኢየሱስ ፡ አለ ፡ የማይጥል ፡ የማይረሳ
ሁሉም ፡ መልካም ፡ ሆኗል ፡ ከእርሱ ፡ የተነሳ

ወዳጅ ፡ ለእኔስ ፡ ወዳጅ
ወዳጅ ፡ ሆነህልኛል
ልቤን ፡ ሀዘን ፡ ጐድቶት
ደርሰህ ፡ አጽናንተኸኛል (፪x)