መልካም ፡ ነው (Melkam New፡) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 2.jpg


(2)

መንግሥትህ ፡ ትምጣ
(Mengesteh Temta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

አምላኬ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ መልካም (፪x)
ጌታዬ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ መልካም (፪x)
መልካም ፡ ነው (፬x)

ስለ ፡ እግዚያብሄር ፡ መልካምነት ፡ ሲሰማ ፡ ማያስችለው
ደግነቱ ፡ ርህራሄ ፡ ማዳኑ ፡ የከለለው
ምሥጋናውን ፡ ይዞ ፡ ይምጥ ፡ በፊቱ ፡ ያፍስሰው
ያማረውን ፡ ቅዱስ ፡ መስአዋት ፡ ለሥሙ ፡ ይሰዋው
በአንድነት ፡ እናክብረው ፡ በመሰንቆ ፡ በዜማ
ፊቱ ፡ እንስገድ ፡ እናሸብሽብ ፡ ዕልልታን ፡ እናሰማ

ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ ተሰብሮ ፡ የዳነ
ክፉን ፡ እንዳይፈራ ፡ በሥሙ ፡ የታመነ
ልዑል ፡ መጠጊያ ፡ የሆነለት ፡ ጋሻ
የታሰበ ፡ ሰው ፡ በዘላለም ፡ ግብዣ

ምሥጋናውን ፡ ይዞ ፡ ይምጥ ፡ በፊቱ ፡ ያፍስሰው
ያማረውን ፡ ቅዱስ ፡ መስአዋት ፡ ለሥሙ ፡ ይሰዋው
በአንድነት ፡ እናክብረው ፡ በመሰንቆ ፡ በዜማ
ፊቱ ፡ እንስገድ ፡ እናሸብሽብ ፡ ዕልልታን ፡ እናሰማ

ከፍ ፡ ከፍ ፡ እናድርገው ፡ መስዕዋታችን ፡ ደስ ፡ ያሰኘው
ጸሎታችንን ፡ ለሰማ ፡ እንዘምረው ፡ የእርሱን ፡ ግርማ

አምላኬ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ መልካም (፪x)
ጌታዬ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ መልካም (፪x)
መልካም ፡ ነው (፬x)

ስለ ፡ እግዚያብሄር ፡ መልካምነት ፡ ሲሰማ ፡ ማያስችለው
ደግነቱ ፡ ርህራሄ ፡ ማዳኑ ፡ የከለለው
ምሥጋናውን ፡ ይዞ ፡ ይምጥ ፡ በፊቱ ፡ ያፍስሰው
ያማረውን ፡ ቅዱስ ፡ መስአዋት ፡ ለሥሙ ፡ ይሰዋው
በአንድነት ፡ እናክብረው ፡ በመሰንቆ ፡ በዜማ
ፊቱ ፡ እንስገድ ፡ እናሸብሽብ ፡ ዕልልታን ፡ እናሰማ

የበረታ ፡ ሰው ፡ በእርሱ ፡ እንባው ፡ ታብሶ
ጌታ ፡ የፈወሰው ፡ በህመሙ ፡ ደርሶ
እንደ ፡ እኔ ፡ ያለ ፡ ምሕረት ፡ ያገኘ
በቸሩ ፡ አምላክ ፡ ካለ ፡ የተጐበኘ

ምሥጋናውን ፡ ይዞ ፡ ይምጥ ፡ በፊቱ ፡ ያፍስሰው
ያማረውን ፡ ቅዱስ ፡ መስአዋት ፡ ለሥሙ ፡ ይሰዋው
በአንድነት ፡ እናክብረው ፡ በመሰንቆ ፡ በዜማ
ፊቱ ፡ እንስገድ ፡ እናሸብሽብ ፡ ዕልልታን ፡ እናሰማ

ከፍ ፡ ከፍ ፡ እናድርገው ፡ መስዕዋታችን ፡ ደስ ፡ ያሰኘው
ፀሎታችንን ፡ ለሰማ ፡ እንዘምረው ፡ የእርሱን ፡ ግርማ