ለምን (Lemen) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 2.jpg


(2)

መንግሥትህ ፡ ትምጣ
(Mengesteh Temta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:15
ጸሐፊ (Writer):
(Tamrat kifle
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

ስንቱ ፡ ያልተገባ ፡ ከፍታ ፡ ረግጧል
ያልዘራዉን ፡ መልካም ፡ አጭዶ ፡ ተዘልሏል
መንገዱ ፡ ተቃንቶለት
ተሳክቶለታል ፡ በሕይወቱ
ሳይለፋ ፡ ምንም ፡ ሳይደክም
ባይተጋም ፡ ሙሉ ፡ ነዉ ፡ ቤቱ
ለፃድቁ ፡ ተከለከለ ፡ በጽድቅ ፡ የዘራዉንም ፡ አጣ
ሕይወቱ ፡ ከፋበት ፡ ተጨነቀ ፡ ያለ ፡ ኃጥያቱ ፡ ተቀጣ
አላልፍልህ ፡ አለዉ ፡ ጨለማ ፡ መንጋቱን ፡ እየናፈቀ
ጥሮ ፡ ግሮ ፡ አላተረፋም ፡ በኪሳራ ፡ ያለዉ ፡ አለቀ

ለምን (፭x)
ለምን ፡ ግን
ለምን ፡ ለምን

የኃይላቸዉ ፡ ጥንካሬ ፡ ብርታታቸዉ ፡ ሲበዛ
በምስኪኑ ፡ ሲሳለቁ ፡ ሲያሳዩት ፡ ጭንቅ ፡ አበሳ
አመፀኞች ፡ ከፍ ፡ ሲሉ ፡ ሳይደክሙ ፡ ሲከናወኑ
ተከታይ ፡ ሲበዛላቸዉ ፡ ፃዲቁን ፡ ግን ፡ ሲኮንኑ

ለምን (፭x)
ለምን ፡ ግን
ለምን ፡ ለምን

እግዚአብሔር ፡ ከቶ ፡ አይባልም ፡ ለምን
የሚሰራዉን ፡ ስለሚመዝን ፡
ፍርድ ፡ የተዛባ ፡ ቢመስልም ፡ እንኳን
አላማ ፡ አለዉ ፡ የእርሱ ፡ ዝምታ

ኃጥአን ፡ በድጥ ፡ ላይ ፡ ናቸዉ
ይፈጥናል ፡ ዉድቀታቸዉ
እግዚአብሄር ፡ ሲነሳ ፡ ከፊት ፡ ነዉ ፡ ጥፋታቸዉ
ለልበ ፡ ንጹሐን ፡ ግን ፡ ቀን ፡ ይወጣላቸዋል
የደረሰባቸዉን ፡ እግዚአብሔር ፡ ተመልክቷል
ፃድቅ ፡ ፃድቅ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፃድቅ
እርሱ ፡ አይሳሳት ፡ ፃድቅ ፡ ነዉ ፡ ፃድቅ