አንተማ ፡ ጌታ ፡ ነህ (Antema Geta Neh) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 2.jpg


(2)

መንግሥትህ ፡ ትምጣ
(Mengesteh Temta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 3:57
ጸሐፊ (Writer):
(Tamrat kifle
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

1. አንተማ ጌታ ነህ እኔ ባገኝ ደግሞም ባጣም
አልጠረጥርህም ባጋጠመኝ እድል እጣ
አንተማ ጌታ ቢሆልኝ ባይሆንልኝ
አባ ወድሃለሁ ካንተ ፍቅር ማን ይለየኝ

አዝ፡-ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ሁኔታዎች አይቀይሩህ ፡
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ለዘላለም ልገዛልህ

2. የትኛዉም ዉጣ ዉረድ በመንገዴ ገብቶ
አንተን እንዳልከተልህ አያደርገኝ ከቶ
ለክብርህ መገዛቴን ጠብቄ ቆማለሁ
 ነገሮች ቢለዋወጡም አንተ ያዉ ነህ አዉቃለሁ

ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ሁኔታዎች አይቀይሩህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ለዘላለም ልገዛልህ

3. ለልጅ የሚያስፈልገኝን አባቴ ታዉቃለህ
ለዉሳኔህ የእኔን ምክር መች ትፈልጋለህ
በከፍታ ብታስኬደኝ በብዙ ብሳካ
ጌታዬ አንተ ብቻ ነህ በድል ያራመድከኝ


ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ሁኔታዎች አይቀይሩህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ለዘላለም ልገዛልህ

4. ተማምኜሀለሁ ጌታ እስከ ዘላለሜ
በጎ ነዉ ሐሳብህ ለኔባይሆን እንኳን ሕልሜ
መሻቴ ባይሞላልኝ ልቤ ባንተ ረካ
ሁሌም የህይወቴ ጌታ ነህ በማንም አትተካ

ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ሁኔታዎች አይቀይሩክ አንተማ ጌታ ነህ አንተማ ጌታ ነህ አንተማ ጌታ ነህ ሁኔታ ማይለዉጥህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ሁኔታ ማይለዉጥህ