Mesfin Gutu/Teshager Yalew/Ante Yenie

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ርዕስ አንተ የኔ ዘማሪ መስፍን ጉቱ Volume 3 አልበም ተሻገር ያለው

አንተ የኔ የራሴ የግሌ የኔ ባስጨናቂው ለት ለኔ ደርሰህ በጨለማዬ ላይ ብርሃን ይብራ ብለህ ታሪኬን ለውጠህ ታዲያ ልበልህ እንጂ አንተ የኔ (፪x)

ማን ኧረ ማን ማን ይወስድብኛል አንተን ከኔ (፪x) ማን ኧረ ማን ማን ይወስድብኛል አንተን ከኔ (፪x) ተማመለህ እኮ ነው የኔ ጌታ በጭንቅ የወለድከኝ በጎልጎታ እድሜዬን በሙሉ ሰጥሃለሁ ዘላለም ለቃልህ እገዛለሁ እገዛለሁ

ታዲያ ልዘምር እንጂ ልቀኝ እንጂ ለባለውለታዬ ልኑር እንጂ አሃሃሃ ታዲያ ታዲያ (፪x)

እንደመሸ አይቀርም ለሊቱ ይነጋል (፬x)

ማንጋት ልማድህ ነውና ማንሳት ልማድህ ነወና ማክበር ልማድህ ነወና ማስዋብ ልማድህ ነውና ውዴ የኔ ነው እኔም ደግሞ የእርሱ ነኝ የየሱስ ነኝ (፪x) ማንም አይገባም በመሀላችን ጉድለት የሌለበት ነው ፍቅራችን ጊዜም ሁኔታም አይሽረዉም ለኔስ ኢየሱሴ ልዩ ነዉ ልዩ ነዉ (፪x)

ታዲያ ልዘምር እንጂ ልቀኝ እንጂ ለባለውለታዬ ልኑር እንጂ አሃሃሃ ታዲያ ታዲያ (፪x)

አንተ የኔ የራሴ የግሌ የኔ ባስጨናቂው ለት ለኔ ደርሰህ በጨለዬ እኔ ላይ ብርሃን ይብራ ብለህ ታሪኬን ለውጠህ ታዲያ ልበልህ እንጂ አንተ የኔ (፪x)

ትምክህቴ ኩራቴ የማምለጫ አለቴ፣ አንተ አይደለህም ወይ እውነተኛ ወዳጄ ትምክህቴ ኩራቴ የማምለጫ አለቴ፣ አንተ አይደለህም ወይ እውነተኛ አባቴ።