Meserete Kristos Choir/Yetamenkuten Awqewalehu/Leul Tewelede

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ልዑል ፡ ተወለደ ፡ በቤተልሔም

የፍጥረታት ፡ ቤዛ ፡ መድኃኒያለም
ክብር ፡ በአርያም ፡ ይሁን ፡ ለእግዚአብሔር
ወድቋል ፡ ከላያችን ፡ የሞት ፡ ፍርሃት ፡ ቀንበር

በግርግም ፡ ተወልዶ ፡ በመስቀል ፡ ሊሰቀል የዓለምን ፡ ሁሉ ፡ ኃጢአት ፡ እርሱ ፡ ለመቀበል አማኑኤል ፡ መጥቶአል ፡ ከአምላክ ፡ ሊያስታርቀን ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን

ከአርያም ፡ ተላከ ፡ የምስራች ፡ ወንጌል በበረት ፡ እንዳለ ፡ የልዑላን ፡ ልዑል በድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ለምንኖር ፡ ሁሉ ብርሃን ፡ ወጥቶልናል ፡ ሃሌሉያ ፡ በሉ

የጥልን ፡ ግድግዳ ፡ ለማፍረስ ፡ ወረደ በበረት ፡ ተወልዶ ፡ እራሱን ፡ አዋረደ ወደረኞቻችን ፡ አዩ ፡ ደስታችንን አማኑኤል ፡ ፅድቃችን ፡ ሆኖ ፡ ሲታደገን

መላዕክት ፡ በሰማይ ፡ ክብርን ፡ ለአምላክ ፡ ሰጡ ሰብአሰገልም ፡ ከሩቅ ፡ አገር ፡ መጡ እጣንና ፡ ከርቤን ፡ ወርቅ ፡ አቀረቡለት በበረት ፡ ለተኛው ፡ ለዓለም ፡ መድኃኒት።