ምሥጋና ፡ ይሁን ፡ ዘለዓለም (Mesgana Yehun Zelalem) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ምስጋና ይሁን ዘላለም

 ለእርሱ የሚሳነው የለም

ምስክር እኔ እሆናለሁ

በሕይወቴ ቀምሻለሁ

    ከጠላት ንክሻ ጌታ አዳነኝ በበረታች ክንድ (2)

       ነፍሴም አመለጠች ከጠላት ወጥመድ

       ገድሉን እያወራሁ ምስጋና ልበል ለጌታ ክብር

       ምስክር ነኝና ላረገው ነገር

 

    ሌት ቀን ካስጨነቀኝ ቅንዓት ተሞልቶ (2)

      በድል አራመደኝ ጌታዬ አውጥቶ

      ከፍ ከፍ ያረገኝ ምስኪኑን እኔን ፈጥኖ ያበረታ

      ምስጋናዬ ይኸው ለውዱ ጌታ

 

    ፍቅሩ እንደ ጅረት ባጥንት የሚፈስ (2)

      ቃሉ ብረታት ያለው ነፍስን የሚያድስ

      ድንጋይ ልቤን አልፎ ዘልቆ ገባና (2)

 

      የዛለውን ጉልበት ዳግም አፀና


Navigation menu